ዜና፡ የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ ተደረገ ፤ ውሳኔው ለህዝቡ ከባድ የነበረውን የኑሮ ውድነት እንዳያባብስ ስጋት ፈጥሯል

ሚኒባስ ታክሲዎች በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ከሚሰጡ የትራንስፖርት ዘዴዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የፎቶ ክሬዲት: Researchgate.com

በብሩክ አለሙ @Birukalemu21

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19/2014 ዓ.ም፡- የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ

ከትላንት መስከረም 18/2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ቤንዚን በሊትር – 57 ብር ከ05 ሣንቲም ፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር – 59 ብር ከ90 ሣንቲም እንዲሁም ኬሮሲን በሊትር -59 ብር ከ90 ሣንቲም እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን የአውሮፕላን ነዳጅ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በነበረበት የሚቀጥል ይሆናል ሲል የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ገልጿል።

አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘረጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ህዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም ተብሏል፡፡

እነዚህ ተሽከርካሪዎች በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ ቤንዚን በብር 41.26 በሊትር እንዲሁም ነጭ ናፍጣን በብር 40.86 በሊትር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አይደረግም ሲል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።

የነዳጅ አዳዮችን በተመለከተም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በመግለጫው “አንዳንድ የነዳጅ አደዮች ከጅቡቲ የተረከቡትን ነዳጅ በተለይ ቤንዚንን በማደያ ላይ በመንግሥት በተተመነው ለተሽከርካሪዎች ዋጋ ከመሸጥ ይልቅ በአሳቻ ሰዓት በበርሜልና በጄሪካን በመቸርቸር እጥረት እንዲፈጠር የሚያደረጉና በቴሌ ብር አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሰው ሠራሽ ችግር የሚፈጥሩ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል” ብሏል፡፡ አክሎም እነዚህ ችግሮች ከመሠረቱ ለመፍታት የሚያስችል ዝግጅት የተደረገ ሲሆን በሁለተኛዉ ምዕራፍ ወደ ተጨባጭ እርምጃ የሚገባ ይሆናል ሲል አስጥንቅቋል፡፡

ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለንብረቶችና ተቆጣጣሪ አካላትም ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ ይደረጋል ያለው መግለጫው የታለመው ድጎማ አሠራሩን ቀልጣፋ ለማድረግ በተዘረጋው የቴሌ ብር ሲስተም በመታገዝ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት የተቻለ መሆኑን ጠቀሶ ባለፉት ሦስት ወራት ከሁለት ቢሊዬን ብር በላይ የነዳጅ ሽያጭ ተፈፅም ተችሏል ብሏል፡፡

መንግስት የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያውን ተከትሎ በእቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለፅ ቢያስጠነቅቅም በሰኔ ወር ላይ ሃሳባቸውን ለአዲስ ስታንደርድ ያካፈሉ የከተማዋ ነዋሪዎች የዋጋው ጭማሬ መኖሩንን በትራንፖርት ላይም ለከፋ እንግልት መዳረጋቸውን ተናግረዋል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት ከሰኔ 29 ቀን ጀምሮ በሊትር ቤንዚን 47 ብር  ከ83 ሳንቲም ፣ ነጭ ናፍጣ 49 ብር ከ02 ሳንቲም ፣  ኬሮሲን ከ49 ብር ከ02 ሳንቲም ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 53 ብር ከ10 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 52 ብር ከ 37 ሳንቲም፣ የአውሮፕላን ነዳጅ 98 ብር ከ83 ሳንቲም ሲሸጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

መንግስት በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረገበት ማግስት ነጋዴውና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በህብረተሰቡ ላይ የራሳቸውን ጭማሬ ሲያደረጉ መቆየታቸው ይስተዋላል፡፡ ይህም ድርጊት ቀድሞውኑ ለህዝቡ ከባድ የነበረውን የኑሮ ውድነት ይባስ እንዳያሻቅብ ስጋት አለ፡፡

መንግስት የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያውን ተከትሎ በእቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለፅ ቢያስጠነቅቅም በሰኔ ወር ላይ ሃሳባቸውን ለአዲስ ስታንደርድ ያካፈሉ የከተማዋ ነዋሪዎች የዋጋው ጭማሬ መኖሩንን በትራንፖርት ላይም ለከፋ እንግልት መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን ተከትሎም አንዳንድ የትራንስፖረት አገልግሎት ሰጪ ያልተገባ የታሪፍ ጭማሪ በማድረግ ተጠቃሚውን ሲያንገላቱ መቆየታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘገባለች፡፡ አሁን የደተረደውን ጭማሪን ተከትሎም ከተፈቀደው ውጭ የዋጋ ጭማሪ ሊደረጉ ስለሚችሉ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቁምነገር እሸቱ ከዚህ በፊት ለአዲስ ስታንዳርድ በሰጡት ቃል መሰረት በተደረገው ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የተነሳ የዋጋ ላይ ግሽበት እንዳይከሰት ከሶስት ወር በፊት የሚቆጣጠር ግብረ-ሀይል ተቋቁሞ ቁጥጥር ለማድረግ ወደ ስራ እንዲገባ መደረጉን ገልፀው ነበር፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.