በብሩክ አለሙ @Birukalemu21
ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም ፣አዲስ አበባ፡- የቡርጂ ልዩ ወረዳ አርሶ አደሮች የዝናብ እጥረት መከሰቱን ተከትሎ ለበልግ የዘሩት ሰብሎች በመውደማቸው በረሃብ እየተጎዱ መሆናቸውን የቡርጂ ልዩ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን አስታወቀ።
የቡርጂ ልዩ ወረዳ አርሶ አደሮች ባለፉት ሁለት ዓመታት በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ዝቅተኛ ምርት መገኘቱነን ገልፀው የዘንድረው ግን የከፋ በመሆኑ እና አፈጣኝ እርዳት ያስፈልገናል ብለዋል። ለቀጣይ መኸር የዘር፣ የግብዓት አቅርቦት እና ሌሎች ድጋፎችን መንግስት እንዲያቀርብም አርሶ አደሮቹ ጠይቀዋል።
የወርዴያ ድንባቾ ቀበሌ አርሶ አደር የሆኑት ወ/ሮ ሃብቦ ዳቶ እንደገለጹት ለበልግ የዘሩት ሰብል በዝናብ እጥረት ሙሉ በመሉ መውደሙን ገልፀው “በቤታችን የሚላስ የሚቀመስ እህል የለም፤ በረሃብ እየተቸገርን ነው፤ መንግስት እና ለጋሽ ድርጅቶች እጃቸውን እንዲዘረጉ እንጠይቃለንም” ብለዋል።
ሌላኛው አርሶ አደር ህርቦ ሻሬና ካሣ ህዶ በዘንድሮው በልግ 10 ሄክታር ማሳ ላይ የተለያዩ ሰብሎችን ዘርተው እንደነበርና በዝናብ እጥረት ሁሉም ሰብሎች መድረቃቸውን ገልፀዋል።
የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽብሩ ኦቴ በዘንድረው ምርት ዘመን 85 ሺህ 6 መቶ 96 ሄክታር መሬት በሰብል ተሸፍነው የነበረ ቢሆንም በዝናብ እጥረት 53 ሺህ 4 መቶ 90 ሄክታር ላይ ተዘርተው የነበረው የተለያዩ ሰብሎች ምርት ሳይሰጡ በድርቅ መጥፋታቸውን ተናግረዋል።
ኃላፊው በምግብ እጥረት እየተቸገሩ ያሉ አርሶ አደሮች የእህል እርዳታ እንዲያገኙ ሪፖርት ማድረጋቸውንና ክልሉም በቀረበው ሪፖርት መነሻ ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም ባለው ነባራዊ ሁነታ ድጋፉ በቂ ስላልሆነ የምስል እና ሌሎች መረጃዎችን ለሚመለከተው አካል ለማድረስ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል። አስ