ዜና፡ የሸዋ ሮቢት ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ሰራተኛ በጥይት ተመታ ተገደለች

ወ/ሪት ጽዮን ተገኝ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14/ 2015 ዓ.ም፡-  የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የስራ ባልደረባ የሆነችው ወ/ሪት ጽዮን ተገኝ ትላንት ምሽት 12 ስአት አካባቢ አቅጣጫው ካልታወቀ ቦታ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቷ ማለፉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

ወ/ሪት ጽዮን  ቤተሰብ ለመጠየቅ በባጃጅ ላይ እያለች በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ግድያው ተጣርቶ ወንጀለኞችን በህግ ቁጥጥር ስር ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ የከተማ አስተዳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫ ገልጧል፡፡

ከተማ አስተዳደሩና መላው ሰራተኛ በወ/ሪት ጽዮን ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ ስርዓተ ቀብሩም በ06 ቀበሌ ቆቦ ቃለ ህይወት ቅዱስ እግዚአብሄር አብ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 7 ስአት አካባቢ ይፈጸማል ብሏል፡፡

የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም   ከምሽቱ 3 ስዓት ገደማ  ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸው ይታወሳል፡፡ 

ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት “የተሰጣቸውን የህዝብ አደራ ለመወጣት ውሎአቸውን በስራ ተጠምደው ለእረፍት” ወደ ቤታቸው ከመኪና ላይ ወርደው ሊገቡ ሲሉ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰባቸው ጥይት መገደለቸውን የከተው አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት  አስታውቆ ነበር።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.