ዜና፡ የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ሊቀመንበር እና ስራ አስፈፃሚ ኃላፊዎችን በመሾም በይፋ ተመሰረተ

የሲፌፓ ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር ተሰማ ኤልያስ ምስል-ሲፌፓ


አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25 2014 ዓ.ም፡- ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ጊዜያዊ የምዝገባ ፍቃድ የተሰጠው የሲዳማ ህዝብን በዋና ምርጫ ክልልነት የሚወክለው የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም  ባካሄደው የምስረታ ጉባኤ ሊቀመንበር እና  ስራ አስፈፃሚ ኃላፊዎችን በመምረጥ በይፋ ተመሰረተ፡፡

በዚህም መሰረት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑትን ተሰማ ኤልያስ የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ረዳት ፕሮፌሰር ተሰማ ለሲዳማ ክልል የሲዳማ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ትግልን በመደገፍ  የሚታወቁ ሲሆን በሲዳማ ክልል አደረጃጀት ጋር በተያያዘ ለአንድ አመት ያህል ታስረዋል።

በተጨማሪም አቶ ፓትሮስ ዱቢሶ ምክትል ሊቀመንበር እና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ደሳለን ደምሴ የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ኃላፊ፣ ወይዘሮ ሙሉ ጋላሳ የሴቶችና ወጣቶች ምክር ሰብሳቢ፣ አቶ ገነነ ሀሳና የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ዶ/ር ፔንግዳሁ አሸንዴ የስልጠናና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ፣  አቶ አብነት ሮራቶ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ኃላፊ፣  አቶ ተመስገን ካቃዎ የምርምር እና ስትራቴጂ ኃላፊ፣ አቶ መሰለ ሀርባቾ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ኃላፊ፣  አቶ እሸቴ ኢፋ  የመገናኛ ብዙሃን እና የህትመት ዘርፍ ኃላፊ፣ አቶ ላድሆ ዮሴፍ  የህግ ጉዳዮች ኃላፊ፣ አቶ አየለ ማራሶ የባህልና ቋንቋ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም አቶ ጻድቁ ሙሴ  የኮሙዩኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በመሆን ተመርጠዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ጊዜያዊ የምዝገባ ማረጋገጫ ሰነድ የተሰጠው ፓርቲው ነሐሴ 10 ባወጣው  መግለጫ፣ “የሲዳማ ህዝብ ከ135 ዓመታት በፊት ጀምሮ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር፣ ባህልና ቋንቋው እንዲከበር ጠንክሮ ሲታገል የኖረ ታጋይ ህዝብ ነው” ያለ ሲሆን  ራሱን የማስተዳደር እውን ያደረገው ደግሞ “በህዝብ መራራ ትግል” መሆኑን ተልፆ በትግሉም  ክልላዊ መንግስት መሆን ችሏል ብሏል። ፓርቲው አክሎም ይህ “ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ መብት በአግባቡ አልተመለሰም። በተግባር አሁን ባለው አገራዊ ሥርዓት ክልሎች የሚተዳደሩት በማዕከላዊ መንግሥት በተሾመ ሥልጣን ነው። ይህም በህገ መንግስቱ የተደነገገው የክልሎች ባለቤትነት/ሉዓላዊነት እየተሸረሸረ በመምጣቱ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ገዥ ፓርቲ ማዕከላዊነት በመያዙ ነው” ሲል መግለፁን አዲስ ስታንዳድ ዘግባለች

የሲዳማ ክልል የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የባህልና የፍትህ ሴክተሮች “ትክክለኛውን መንገድ አልተከተሉም” እየተባለ  ሲሆን  ክልሉ ምክንያታዊነት የጎደለው “የስራ አጥነት ቀውስ፣ የፍትህ እጦት፣ ሙስና፣ ጎሰኝነት፣ አድሎና አድሎአዊ ድርጊቶች እየተስተዋለ ነው” ሲል ፓርቲው  ተችቷል። አክሎም ይህ  “የማግለል ፖለቲካ ስርዓት” ነውም ብሎታል፡፡

የሲዳማ ህዝብ ትግል መሰረታዊ ዓላማን እውን ለማድረግና ህዝቡ እየደረሰበት ያለውን ችግር ለመቅረፍ ህዝቡን አደራጅቶ የሚታገል ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ ባለመኖሩ  ህዝቡ ለከፋ ችግር እንዳይጋለጥ ጥቅሙን የሚያስከብረለት ተገዳዳሪ ያስፈልጋል ሲል በመግለጫው አብራርቷል።

ሲፌፓ የተቋቋመው “የህዝባችን መሰረታዊ ጥያቄዎችን” ለመመለስ መሆኑን ገልጿል። አክሎም ምስረታውም አሁን ባለው እውነታ በሚፈለገው ደረጃ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ለማካተት የተደራጀ የፖለቲካ ፓርቲ አስፈላጊ ሆኗል ብሏል። በተጨማሪም “በዴሞክራሲያዊ እሴቶች፣ ዴሞክራሲያዊና ህዝባዊ የስልጣን ባለቤትነትን ተግባራዊ ለማድረግ ለመታገል፣ በብዝሃነት እና በውይይት በማመን፣ እውነተኛ ሀገራዊ ፌደራሊዝምን በመከተል እውን ለማድረግ ተመሳሳይ ግብ ካላቸው ብሄራዊ ፓርቲዎች ጋር ይሰራል” ሲል የፓርቲውን አስፈላጊነት ገልጿል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.