ዜና፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ ሁለት የፖሊስ አዛዦች በጥይት ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27/ 2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ የሆኑት ም/ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ወርቁ ሽመልስ ትላንት ሰኔ 26፣ 2015 ለስራ በወጡበት ለጊዜው ማንነቱ ባልታወቀ አካል በተከፈተባቸው ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አስታወቀ፡፡

የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫ አብሯቸው መኪና በማሽከርከር ላይ የነበረ አንድ የፖሊስ አባል ቆስሎ ህክምና እየተደርገለት እነደሚገኝ ገልጧል፡፡

የፖሊስ አዛዦቹ ላይ ጥቃቱ የተከፈተባቸው ትላንት ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት አካባቢ በደጀን ወረዳ ኩራር ቀበሌ ደምበዛ ጎጥ የሚሰጠውን የ8ኛ ክልላዊ ፈተና የጸጥታ ስራ ለመከታተል በወጡበት መሆኑን የወረዳው አስተዳደር ገልጧል፡፡ አስተዳደሩ ወንጀለኞቹን በአጭር ጊዜ ለህግ ለማቅረብ ጠንክሮ የሚሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ህይወታቸውን ላጡት አዛዦች የተሰማውን ሀገን የገለፀው የወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት፣ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ሲሉ መስዋዕት የሆኑ የፀጥታ አካላት ቤተሰቦችን አስተዳደሩ እንደራሱ አድርጐ የሚንከባከብና የሚደግፍ ይሆናል ሲል አስታውቋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.