ዜና፡ ከቤተ እስራኤላዊ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወሲብን እንደመደለያ ተጠቅመው ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስመጡ አድርገዋል የተባሉ የእስራኤል ባለስልጣን ተከሰሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5/2015 ዓ.ም፡- ሊዮር ሰለሞን የተባሉ የእስራኤል ባለስልጣን ከስድስት ቤተ እስራኤል ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር የወሲብ ግንኙነት በመፈጸም ቤተሰቦቻቸውን ከኢትዮጵያ ለማስመጣት እንዲፈቀድላቸው አስቸለዋል በሚል መከሰሳቸውን ጀሩሳሌም ፖስት በድረገጹ አስነብቧል።

ባለስልጣኑ ከስድስት ሴቶች ጋር ወሲብ ቢፈጽሙም የተከሰሱት በሶስቱ መሆኑን ያስታወቀው ጋዜጣው ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ደግሞ የዘጠኝ ወር የማህበረሰብ አገልግሎት ብቻ መሆኑን ገልጿል። ሊዮር ሰለሞን  የእስራኤል ከፍተኛ የህዝብ እና ኢሚግሬሽን ባለስልጣን መሆናቸውን የጠቆመው የጋዜጣው ዘገባ ሴቶቹ ቤተሰቦቻቸውን ከትውልድ ሀገራቸው እንዲያስመጡ ወሲብ ግንኙነትን እንደ መደለያ የመቀበሉን ሀሳብ ያመነጩት ባለስልጣኑ መሆናቸውን አመላክቷል። ሴቶቹ ይህን ተግባር ለመፈጸም ያስገደዳቸው በኢኮኖሚ ችግር ላይ መሆናቸው እና በእስራኤል ቤተሰብ ስለሌላቸው መሆኑን በፍርድ ቤቱ መገለጹን ድረገጹ በዘገባው አካቷል። ሊዮር ሰለሞን የወሲብ ጉቦ ተቀብለዋል ከሚለው ክሳቸው በተጨማሪ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ዳታ ቤዝ በመጠቀም የግለሰቦችን መረጃ ለማወቅ ህግ ጥሰዋል እንደቀረበባቸው አመላክተዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.