ዜና፡ አቡነ ማትያስ እና ሉዑካቸው በመቀሌ አቀባበል ያልተደረገላቸው ምንም አይነት የተጻፈልን ደብዳቤም ይሁን የተያዘ መርሃ ግብር ስላልነበረ ነው ስትል የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ቤተከርስቲያን ሲኖዶስ አባላትን ያካተተው በአቡነ ማትያስ የተመራው ሉዑክ በመቀሌ አቀባበል ያልተደረገለተ ምንም አይነት የተጻፈልን ደብዳቤም ይሁን የተያዘ መርሃ ግብር ስላልነበረ ነው ስትል የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስታወቀች።

የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተ ክህነት ጸሐፊ መጋቤ ብርሃናት ተስፋየ ሀደራ ለትግራይ ቴሌቪዥን እንደገለጹት ለቤተክህነቱ ስለ ጉብኝቱ ያሳወቀው አካል የለም ሲሉ ተናግረዋል። በቀጥታ ለመንበረ ሰላማ የተጻፈ ደብዳቤ አልነበረም፤ የተያዘ መርሃ ግብርም አልነበረም፤ እሽታችን እና እምቢታችን ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ነው እንግዶቹ ወደ መቀሌ የመጡት ሲሉ ተደመጠዋል።

ቅዱስ አባታችን እዚህ ስለመጡ ወይንም ስላልመጡ ሳይሆን ባሉበት ሁነው እሳት በሚነድበት ወቅት ስለኢትዮጵያ ህዝብ ያለቀሱ፣ የተናገሩ፣ ድምጻቸውን ያሰሙ አባት ናቸው፤ ለዚህም ትልቅ ክብር አለን ያሉት ጸሐፊው ብጹዕነታቸውም ይህን ያውቃሉ፣ እነሱም እሳቸውን የላኳቸው ሆን ብለው ለመፈተን ነው፣ የትግራይ ተወላጅ ስለሆኑ ሊቀበሏቸው ይችላሉ በሚል የተሳሳተ ግምት ነው ብለዋል። ብፁእ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስን ሽፋን አድርጎ የህዝቡን ቅሬታ እና ሐዘን ለማድበስበስ ያለመ ነው ሲሉ መግለጻቸውን ዘገባው አካቷል።

እርቅ የቤተክርስቲያናችን መርህ ነው፣ ይህንን ያስተማረችውም የትግራይ ቤተክርስቲያን ናት ያሉት መጋቤ ብርሃናት ተስፋየ ሀደራ ይሁንና ቅሬታ እንዲፈጠር እና የትግራይ የሀይማኖት አባቶች እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ያደረጋቸውን ጥቃት በመዘርዘር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሲኖዶሱ አባቶች ልባዊ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል።   

በሌላ ዜና ከአውስትራሊያ ወደ መቀሌ ሲያቀኑ የነበሩት ቆሞስ ኣባ ሰረቀብርሃን ወልደሳሙኤል በአዲስ አበባ ኤርፖርት እንዳየወጡ መደረጋቸውን ይታወቃል ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት ቆሞስ ኣባ ሰረቀብርሃን ወልደሳሙኤል በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች አስገዳጅነተ ወደ ሀንድ እንዲጓዙ ተደርገዋል ተብሏል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.