አዲስ አበባ፤ ጥቅምት፣10/2015 ዓ.ም፡- ባለፈው ሳምንት አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ 3,310 አባወራዎች (16,550 ግለሰቦች) አስፈላጊ የቤት ቁሳቁሶችን ማከፋፈሉን አስታወቀ።
እርዳታው በምዕራብ ኦሮሚያ ጃርዴጋ ጃርቴ እና በአሙሩ ወረዳዎች ስር ከሚገኙ ከ14 ቀበሌዎች ለተፈናቀሉ ግለሰቦች ነዉ የተከፋፈለዉ።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) ፣ በአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎች እና በታጠቁ ግለሰቦች ማንነት ላይ ተመስርቶ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ100 በላይ ንፁሀን ዜጎችን ተገድለዋል።
የኮሚሽኑ ሪፖርት እንደሚያመላክተው በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፣ ዘረፋ ተፈፅሟል፣ የግል ንብረትም ወድመዋል።
በወቅቱ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር በስልክ ቆይታ ያደረጉት አንድ የሻምቡ ከተማ የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ ግለሰብ እንደገለፁት ጥቃቱን ሸሽተው ከነበሩት መካከል በርካቶቹ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነቸው ሻምቡ ከተማ መድረስ ችለዋል።
ከዚህ ቀደም ጳጉሜ 1 ቀን ከ60 በላይ የሚሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች በአሙሩ ወረዳ በአገምሳ፣ ጆግ ሚጊር፣ ታም ኢላሙ፣ ጀቦ ዶባን፣ ጦምቤ ዳነጋቤ፣ ጃዋጅ፣ ግናሬ፣ ለገ ሚቻ፣ ሉቁማ እና ዋሌ ቀበሌዎች (ትናንሽ ወረዳዎች) በነሀሴ 24 እና 25 በጅምላ ተገድለዋል። ኢሰመኮ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ ከአካባቢው የተሰባሰቡ ታጣቂዎች እና ከአማራ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በመጡ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል። ከ20,000 በላይ ሰላማዊ ዜጎችም ተፈናቅለዋል። አስ