ትንተና፡- እየጨመረ ባለው የትምህርት ዋጋ ወላጆች ፈተና ውስጥ ባሉበት ወቅት፣ ጦርነትና የተፈጥሮ አደጋዎች በኢትዮጵያ 13 ሚሊዮን ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት ውጪ አድርገዋል

የምስል መግለጫ፡ በትግራይ የሚገኘው የመንጊ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጥቅምት ወር 2014 ለህፃናት በሩን ከፍቷል።እንደ ዩኒሴፍ ዘገባ “ምንም እንኳን ጉዳቱ ቢኖርም ፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች እንደገና እየተከፈቱ ነው እና ዩኒሴፍ እና አጋሮች ልጆችን ወደነበሩበት ክፍል እየመለሱ ነው” የምስል ክሬዲት፡ ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ/2015።

በምህረት ገ/ክርስቶስ እና በአሰፋ ሞላ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት፣10/2015 ዓ.ም፡- በሀገሪቱ በተከሰቱ ጦርነቶች፣ ድርቅና ጎርፍ ሳቢያ 13 በሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (UNOCHA) ባሳለፍለው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።

ለአብነትም በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ 125 ትምህርት ቤቶች በመውደማቸው 70,000 ህጻናት ከትምህርት ገበታ የተፈናቀሉ ሲሆን በአማራ ክልል በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ457 በላይ ትምህርት ቤቶች ወድመው ወደ 200,000 የሚጠጉ ህጻናት ወደ ትምህርት እንዳሄዱ ሆኗል ሲል ሪፖርቱ ያትታል፡፡

በአጠቃላይ 13 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች 2.93 ሚሊዮን የሚሆኑ ህፃናት በጦርነትና ድርቅ ምክንያት ከትምህርት ውጭ መሆናቸውን ሪፖርቱ አክሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት እንደሚያመላክትው ከሆነ 2.53 ህፃናት ሚሊዮን ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉት በጦርነት ምክንያት ሲሆን 401 ሺ የሚሆኑ ህፃናት በድርቅ ምክንያት መፈናቀላቸው ነው የተገለፀው፡፡ በተጨማሪም 85 ፐርሰንት በትግራይ ክልል የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና በአፋር እና በአማራ ክልል የሚገኙ 4ሺ 400 መቶ ትምህርት ቤቶች ወንበርና ጥቁር ሰሌዳ እንደሚያስገልጋቸው ጭምር ነው የተባበሩት መንግስታት በሪፖርቱ ያካተተው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው ለ2015 የትምህርት ዘመን በአገሪቱ 29 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታልሞ የነበረ ቢሆንም፣ ሊመዘገቡ የቻሉት ግን 16 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ይህም በዓመቱ ይመዘገባሉ ተብሎ ከታቀደው 55 ነጥብ 6 በመቶ ብቻ እንደሆነ ታውቋል።

ቀሪ 45 በመቶ ገደማ መማር የሚችሉ ተማሪዎች ለመማር የሚያስችላቸውን ምዝገባ አላከናወኑም።

በያዝነው ወርሃ መስከረም ላይ ተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በኩል በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ተማሪዎች አሃዝ መጠን ይፋ ያደረገ ሲሆን በኢትዮጵያ ቢያንስ ከ6 እስከ 18 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 10 ሚሊዮን የሚገመቱ ህጻናት በትምህርት ገበታቸው ላይ አንደሌሉ በሪፖርት ገልጿል።

ዩኔስኮ ኢትዮጵያን ተማሪዎች በጊዜ ወደ ትምህርት ገበታ ያለተመለሱባቸው አምስት ሃገራት ተርታ ውስጥ ኢትዮጵያን በቀዳሚነት ደርጃ ላይ አስቀምጧታል።

ዩኔስኮም በትግራይ ክልል ባሉ ትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ለመሄድ ስጋት እንዳላቸው ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ በጦርነት ምክንያት በትምህርተ ስርዓቱ የደረሰ ጉዳትን የገመገመ ሲሆነ በምእራብ እና ሰሜናዊ ዞኖች በታጣቂ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ካሉ ትምህርት ቤቶች በስተቀር በስድስት ዞኖች የሚገኙትን ትምህርት ቤቶች በሙሉ ይመለከታል። ትምህርት ቤቶች፣ የትምህርት ቤት ቁሳቁሶች፤ እንደ ኮምፒውተሮች ያሉ አስፈላጊ መሣሪያዎች ወድመዋል ተብልዋል። ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ያሉት ህጣናት ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም በጦርነት ምክንያት ግማሹ በተቃጠለ ክፍል ውስጥ እየተማሩ መሆኑን ነው የተገለጠው። ግጭቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን እና ተማሪዎች በአሳዛኝ ሁኔታ መሞታቸውን አክሎም ገልጿል።

በተጨማሪም በ2013 90 በመቶ አድጎ የነበረው የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጥር ወደ 21 በመቶ ዝቅ ማለቱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ያወጣው መረጃ ያመላክታል። ከጦርነት ጋር ተያይዞ የሚመጡ ጉዳቶች ፍራቻ ክፍል ውስጥ ገብተው መማርም ሆነ ማስተማር ከባድ እንደሆነም ጭምር ነው የክልሉ ትምህርት ቢሮ የገለጸው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሃገሪትዋ ክፍል ወደ ትምህርት ቤት ገበታቸው ያለተመለሱ ህጻናት በትክክለኛው አድሜያቻው ወደ ትምህርት ገበታቸው ባለመመለሳቸው በራሳቸውና በሃገር ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳቶች አንደሚኖረው በተለያዩ ዘርፍ ሚገኙ ሙሁራን ሲናገሩ ይስተዋላል።

የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር አረጋ ይርዳው ተማሪዎች በጦርነት ሆነ በተለያዩ ሀገር ዉስጥ ባሉ ችግሮች ትምህርት ሲያቇርጡ በሰዓቱ መማር ያለባቸው ሳይማሩ ይቀራሉ ይህም እንደ አንድ ትልቅ ችግር ሊታይ ይችላል ሲሉ ሀሳባቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል። በተጨማሪም ሰላማዊ የሆነ አዕምሮ አይኖራቸው፣ ሁሉ ጊዜ አዕምሯቸው ይረበሻል፣ ትምህርቱም በቀላሉ ሊረሱት ይችላሉ እንዲሁም ቀጣይነት ያላቸዉም ነገር ላይሰሩ ይችላሉ ብለዋል።

ዶክተር አረጋ አክለው ለሁሉም ነገር መሰረት ትምህርት ስለሆነ የተማሪዎች ከትምህርት መቅረት ጉዳቱ በተማሪዎች ላይ በቻ ሳይሆን በወላጆችና በሀገርም ላይ ጭምር ነው፤ ተማሪዎች በጊዜያቸው ትምህርታቸውን ጨርሶ ሃገሪትዋን መጥቀም ሳይችሉ ይቀራሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ እንድ ምሁር፤ በሃገሪትዋ ላይ የተጋረጡ የተለያዩ የሃገር ውስጥ ችግሮች በተለይም በጦርነት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የሚቀሩ ተማሪዎች የተለያዩ የስነልቦና ችግሮች ሊገጥሟቸው እንደሚችል ጠቁመዋል።

በተማሪዎች ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮች መካከል በዋናነት ተስፋ መቁረጥ፤ ከቤተሰብና በማህበረሰብ ጋር ጤነኛ ያልሆነ ግንኝነት፤ ቁጣ እንዲሁም ብስጭት ዋንኞቹ ናቸው ያሉት ምሁሩ በተለይም ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት ከትመህርት ገበታቸው ከተፈናቀሉ በማህበረሰብ ግፊት፣ በታጣቂዎች ግፊት ጦርነትን የመቀላቀል እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል። ምሁሩ ተማሪዎች ተስፋ ከሞቀረጣቸው የተነሳ ውጤታማ ያልሆነ ትውልድ ስብስብ እንዳይፈጠር እና የተማረ ትውልድ እንዳናጣ ስጋት እንዳላቸውም ተናግረዋል።

ምሁራኑ አንደ አንድ መፍትሄ ያስቀመጡት በተለያዩ የሃገሪትዋ ክፍሎች ያለዉ ግጭቶች መፍትሄ ተበጅቶለት ሰላም ሲሰፍን ነው፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ተማሪዎቹ የተረጋጋ አዕምሮ ሳይኖራቸው ትምህርታቸውን ሊቀጥሉ እና ፍሬያማ ሊሆኑ አንደማይችሉ ነው የገለጹት።

የዘንድሮው የትምህርት መሳሪያ የዋጋ ንረት በወላጆች ላይ ያስከተለው ተፅዕኖ በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የመማሪያ ቁሳቁስ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ ተደርጎበት ሲሽጥ ሰንብቷል፡፡ ይህም የወላጆችን የመግዛት አቅም ፈትኗል፡፡

ደብተር በዚህኛው አመት የወርቅ ዋጋ ሁኖብኛል፤ ግዴታ ልጆቼን ማስተማር ስላለብኝ ነዉእንጂ ደብተር ለመግዛት እማወጣው ወጪ ስንት የቤት ቀዳዳ ይሸፍንልኛል”

አዲስ ስታንዳርድ በፒያሳ አከባቢ ባደረገችው ቅኝት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በኩል ለተለያዩ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ በሽፋናቸው ላይ የመስተዳድሩ ሎጎ (መለያ ምልክት) ያላቸው የደብተሮች በነጋዴዎች እጅ ገብቶ ለህብረተሰብ ሲሸጥ ተመልክታለች፡፡

አዲስ ስታንዳርድ ባደረገችው ቅኝት ጀማል መሀዲ ለልጆቹ ደብተርና ሌሎች የትምህርት ቤት ቁሳቁሶችን ለሟሟላት ፒያሳ አከባቢ ሲገዛ ካገኘናቸው ወላጅ አንዱ ነው፡፡ ጀማል የሶትልጅ አባት ሲሆን በአንድ ድርጅት በዝቅተኛ ገቢ ተቀጥሮ ራሱንና ቤተሰቦቹን ያስተዳድራል፡፡ አቶ ጀማል ሶስት ልጆች ያሉት ሲሆን ሁለቱ ልጆቹ የእንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲሆኑ የመጨረሻው ልጁ የአፀደ ህፃናት ተማሪ ነው፡፡

“ደብተር በዚህኛው አመት የወርቅ ዋጋ ሁኖብኛል፤ ግዴታ ልጆቼን ማስተማር ስላለብኝ ነዉእንጂ ደብተር ለመግዛት እማወጣው ወጪ ስንት የቤት ቀዳዳ ይሸፍንልኛል ፤ መንግስት እንደት ይህንን መቆጣጠር ያቅተዋል” ሲል ጀማል በምሬት ይናገራል፡፡

አዲስ ስታንዳርድ በተለያዩ የከተማዋ አከባቢ ተዘዋውሮ የደብተር ዋጋን በቃኘበት ሜክሲኮ፤ ፒያሳ፤ ካዛንችስ እና ቦሌ አካባቢዎች እንደየ ቦታው የተለያየ የመሸጫ ዋጋ የተመለከቱ ሲሆን በሜክሲኮ፤ ፒያሳና ካዛነችስ ተመሳሳይ ሲሆን በቦሌ ግን ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተመልክተዋል፡፡

በስፋት ራዲካል፤ ሲነርላይን እና ኦርቢት የሚባሉ የደብተር አይነቶች በገበያ ላይ የሚገኙ ሲሆን ፤ ዋጋቸውም እንደ ጥራታቸው እንደሚለያዩ በገበያው ላይ ያሉ ነጋዴዎች ያስረዳሉ፡፡

በገበያው ላይ ያለ የቁሳቁሶቹ ዋጋ ስንመለከት ሲነር ላይን ተብሎ የሚጠራው ባለ ሃምሳ ገፅ አንድ ፍሬ ደብተር በገበያ ላይ ከ 60 አስከ 70 ብር ፤ በደርዘን ደግሞ አስከ 780 ብር እየተሸጠ ሲሆን ራዲካል በፍሬ ከ100 እስከ 105፣ በደርዘን እስከ 1200 ብር እንዲሁም ኦርቤት ከ 68 እስከ 95 ብር በፍሬ በደርዘን 960 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ ይህ ከአምናው የደብተር ዋጋ ሲነፃፀር አንድ ሁለተኛ የዋጋ ጭማሬ ማሳየቱን የተማሪ ወላጆች ይገልፃሉ፡፡

“ለልጆቻችን የሚያስፈልገው ደብተር ብቻ ሳይሆን ቦርሳ፤ ዩኒፎርምና ሌላ የትምህርት ቤት ቁሳቁሶች ጭምር በመሆኑ ገና ሌላ አቃ ሳልገዛ በደብተር ብቻ ብሩ ያልቃል” ሲል ጀማል አክሎ ይናገራል፡፡ አቶ ጀማል “ትምህርት ከተጀመረ ቀናትን አስቆጥሯል ግን ለደብተር የሚበቃ ብር ስላልነበረኝ ለልጆቼ ለትምህርትቤት ሚያስፈልጋቸው ነገሮች በጊዜ ማቅረብ አልቻለኩም በዚህም ምክንያት ልጆቼ ራሳቸውን ከሌላው ተማሪ በማስተያየት በሞራል ሊጎዱ ይችላሉ” ሲል አክሏል፡፡

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መጀመሪያ ለአንድ ፍሬ ደብተር ዋጋ ከ40 እስከ 50 ብር ይሸጥ እንደነበር እና የዋጋ ጭማሬው በደብተር ብቻ ሳይሆን በሁልም ለተማሪዎች አስፈላጊ በሆኑ ግብአቶች ላይም ማለትም ዩኒፎርም፣ ደብተር፣ ምሳ ዕቃና፤ እስክርቢቶ፤ ላፒስ እና ሊሎች አስፈላጊ ሚባሉ አቃዎች ላይ ጭምር መሆኑን ወላጆች ይገልፃሉ፡፡

አቶ ገመቺስ ዋንጋሪ በፒያሳ አከባቢ በአንድ የስሁፍ መሳሪያ መደብር ተቀጣሪ ሰራተኛ ሲሆን የትምህርት ቁሳቁሶች ዋጋ ለወላጆች ብቻ ሳይሆን ለነጋዴም አስቸጋሪ መሆኑን አስረድቷል፡፡ አቶ ገመቺስ አክሎም በምሳሌ ሲያስረዳ ደብተርን ብንወስድ ከመወደዱ በተጨማሪ በገበያ ላይም በጣም እጥረት አለ፤ እኛም ስናመጣው በፍለጋ ነው አንዳንዴ ይህም የሚታጣበት ጊዜ አለ ይላል፡፡

ለልጆቼ ዩኒፎርም ሳልገዛ የቆየሁት ይቀንሳል የሚል እምነት ስለነበረኝ ነበር ግን ጭራሹንም እየባሰበት ነው”

በቦሌ አከባቢ ለልጆችዋ ዩኒፎርምና ሌሎች ቁሳቁሶች ስትገዛ ያገኘናት የሁለት ልጆች እናት አለሚቱ መኮንን ገበያው ከአምናው ጋር በማነፃፀር እጅግ በጣም ውድ ነው ስትል ትናገራለች፡፡ “ለልጆቼ ዩኒፎርም ሳልገዛ የቆየሁት ይቀንሳል የሚል እምነት ስለነበረኝ ነበር ግን ጭራሹንም እየባሰበት ነው” ስትል ቅሬታዋን አካፍላናለች፡፡

አለሚቱ በ2014 ዓ.ም የትምርት ዘመን የነበረው የዩኒፎርም ዋጋ አሁን ካለበት ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ እንደጨመረ ስትገልፅ ሱሬ 450 የነበረው አሁን 900፤ ሸሚዝ 300 የነበረው አሁን 750፤ ሹራብ 400 የነበረውን አሁን 750 ሆኗል ብላለች፡፡ አለሚቱ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፀችው ከሆነ አምና ኢቮ የተባለው የሃገር ውስጥ የዩኖፎርም አምራች ድርጅት ነበር የምትገዛው አሁን ግን በጥሬ እቃ እጥረት ምክንያት አስፈላጊ የልጆች ቁሳቁስ ማምረት አልቻለም፡፡

“መንግስት ከውጭ ሚመጣው አቃዎችን በማስቀረት ሃገር ውስጥ ለሚያመርቱ ማበረታት አለበት አለበለዝያ እንኳን ለዩንፎርም ለልጆቻችን ምግብ ያሳስበናል” ትላለች አለሚቱ፡፡ አኔንና መሰሎቼ በዝቅተኛ ገቢ የምንተዳደር ወላጆች የትምህርት ቤት ቁሳቁሶች ዋጋው አኛን ያማከለ ባለመሆኑ መንግስት በተቻለው አቅም ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ በማድረግ ወይም ሃገር ውስጥ እንዲመረት በማድረግ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማምጣት አለበት ሲል ጀማል ተናግሯል፡፡

ልጆቻቸውን በመንግስት ትምህርት ቤት ሚያስተምሩ አንዳንድ ወላጆች እንዳሉት በመንግስት ደረጃ ለልጆቻችን የዩኒፎርምና ሌሎች የትምህርት ቤት ቁሳቁስ ቢሰጣቸውም አሁንም ግን በጣም ዉስን መሆኑን ገልጾው ለምሳሌ ደብተር ላንዳንድ ተማሪ ሲሰጥ ላንዳዶች ተማሪዎች ግን እንዳልደረሳቸውም ነው የተናገሩት፡፡

በሃገሪትዋ በተለያዩ ክልሎች ያለው ጦርነት ምክንያት ብዙ የትምህርት ቁሳቁስ አምራች ፋብሪካዎች የምርት አገልግሎት መስተጠት በማቆማቸው እንደ አንድ የዋጋ ግሽበት መንስኤ ሊታይ ይችላል

የትምህርት ቤት ቁሳቁስ ዋጋ ግሽበት ልብቻው ወቅቱ ጠብቆ የተከሰተ ሳይሆን ከሌሎች ሸቀጦች ጋር ተያይዞ የመጣ ነው ይላሉ በሰላሌ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ አስተማሪ የሆኑት አቶ አዲሱ አበባው፡፡ እንደሳቸው አገላለስ የትምህርትቤት ቁሳቁሶች ደብተር፤ ስክርቢቶ፤ ቦርሳና የመሳሰሉት ቁሳቁሶች በስፋት በውጭ ምንዛሬ ወደ ሃገር ቤት ስለሚገቡ ዋጋቸው ከማህበረሰቡ ጋር ላይ ላይመጣጠን ይችላል፡፡

በተጨማሪም የሃገር ውስጥ ሃብት አሟጦ አለመጠቀም ከፍተኛ የሆነ ግብአቶችና ቁሳቁሶች ከውጭ ሃገር እንድናስገባ ሰለሚያስገድደን እንደ አንድ የቁሳቁስ ዋጋ መናር ምክኝያት ሊሆንም ይችላላ ብለዋል፡፡

በሃገሪትዋ በተለያዩ ክልሎች ያለው ጦርነት ምክንያት ብዙ የትምህርት ቁሳቁስ አምራች ፋብሪካዎች የምርት አገልግሎት መስተጠት በማቆማቸው እንደ አንድ የዋጋ ግሽበት መንስኤ ሊታይ ይችላል ብለዋል አቶ አበባው፡ ፡

ስለዚህ ጉዳይ ጊዜያዊ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው አቅመ ደካማ የሆኑት የማህበረሰብ አካላት የቁሳቁስ ማሰባሰብ መርሃ ግብር በማዘጋጀት እንዲረዱ ማድረግ ሲሆን ዘላቂ መፈተሄው የሃገር ውስጥ ሃብት አሟጦ መጠቀም የተለያዩ የደብትር፤ ስክርቢቶ፤ ዩኒፎርም እንዲሁም ተመሳሳይ ከውጭ እንዲገቡ ኣይገባቸው ቁሳቁሶችን ሃገር ውስጥ እንዲ መረቱ ማድረግ ተገቢ ነው ይላሉ አቶ አበባው፡ ፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተመዘገበው አማካይ የምግብ ዋጋ ግሽበት 40.2 በመቶ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶች የነበራቸው የዋጋ ግሽበትም 25 ከመቶ እንደነበር የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ለችርቻሮ ዋጋ ጥናት የሚያግዙ 119 የተመረጡ የገበያ ቦታዎች መሠረት ተደርጎ የሚቀርበው የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ የሐምሌ 2014 ዓ.ም. ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱም ሆነ ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆነው የግሽበት ሁኔታ አሁንም በ30ዎቹ በመቶ ውስጥ ይገኛል፡፡

የዋጋ ግሽበት በዚህ ጊዜ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ባደጉ አገሮች ጭምር ፈተና እየሆነ መምጣቱን ያስታወቀው የስታትስቲክስ አገልግሎት፣ ‹‹ካለው ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ የኢኮኖሚ ሁኔታና ሌሎች ፈታኝ ሁኔታዎች አንፃር በሐምሌ 2014 ዓ.ም. የታየው የዋጋ ግሽበት መልካም የሚባል ነው፤›› በማለት ገልጾታል፡፡

በሐምሌ ወር የምግብ ኢንዴክስ ክፍሎች መጠነኛ መረጋጋት ማሳየታቸውን የሚሳየው የአገልግሎቱ ሪፖርት፣ በአንፃሩ ምግብ ያልሆኑ የኢንዴክስ ክፍሎች ላይ የሚስተዋለው ጭማሪ አሁንም እያሻቀበ እንደሚገኝ ያመላክታል፡፡

ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉትና ዋና ምክንያቶች ተብለው ከተጠቀሱት ውስጥ በአልኮልና በትምባሆ፣ በልብስና ጫማ፣ የቤት መሥሪያ ዕቃዎች ተብለው በሚመደቡት የቤት ኪራይ፣ ሲሚንቶ፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ የቤት ዕቃዎች፣ ነዳጅ፣ ሕክምናና ጌጣ ጌጦች የተመዘገበው የዋጋ ንረት ይጠቀሳል፡፡

በጠቅላላው የሐምሌ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠን 33.5 በመቶ የምግብ ዋጋ ግሽበት 35.1 በመቶ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 30.4 በመቶ ሆነው መመዝገባቸውን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት ሪፖርት ያሳያል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.