አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2015 ዓ.ም፡- ያሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ በናይጀሪያ በሚሰራጩ በርካታ መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ የነበረው ጉዳይ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ እና የናይጀሪያ አየር መንገድ አርማ ተቀብቶ በረራ ያካሄደው አውሮፕላን ነበር። የናይጀሪያ መገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቁት ከሆነ የሀገሪቱን አርማ አዝሎ ከአዲስ አበባ በመነሳት ናይጀሪያ አቡጃ የገባው ቦይንግ አውሮፕላን ንብረትነቱ የናይጀሪያ አየር መንገድ ሳይሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። ከአስራ አንድ አመት በፊት የተገዛ እና የተመዘገበበት መለያም ET-APL መሆኑን ጠቁመዋል።
የራሱ ባልሆነ አውሮፕላን አርማውን አዝሎ ወደ ናይጀሪያ በረራ ማድረጉን ደርሰንበታል ያሉት መገናኛ ብዙሃኑ የሀገሪቱ መንግስት ምርመራ እንዲያካሄድ በመወትወት ላይ ይገኛሉ።
የናይጀሪያ አቪየሽን ሚኒስትርን ጨምሮ በርካታ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የናይጀሪያ አየር መንገድ ከብዙ ልፋት በኋላ በሰማይ ላይ ከፍ ብሎ በረረ በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ጮቤ መርገጣቸውን እየጠቀሱ መገናኛ ብዙሃኑ የሰው ጌጥ አያስጌጥ ሲሉ ተሳልቀዋል። አውሮፕላኑ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሰ አርማውን መቀየሩ የማይቀር ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የናይጀሪያ የጸረ ሙስና ተቋማት የሀገሪቱ መንግስት በአቪየሽን ሚኒስትሩ ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውም ተዘግቧል። ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል። አስ