“ከለውጡ በኋላ ፈተና በዝቷል ለተባለው እውነት ነው ፈተና በስቷል ግን ደግሞ ተፈናው እያዳከመን ሳይሆን እንደ ወርቅ አጠንክሮ እያወጣን ነው” –ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
አዲስ አባባ፣ ሰኔ 29 /2015 ዓ.ም፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት 6ኛውን፣ 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 28ኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ በስብሰባቀው ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከተነሱ በርካታ ጥያቄዎች መካከል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ያነሱት አንዱ ነው፡፡
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ጀምሮ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገሩን ገልፀው ብልፅግና መራሹ መንግስትም ሆነ ፓርላማው አገራችን ከገባችነት የፖለቲካ ቅርቃብ ማውጣት ስለማይችሉ ስልጣንዎን ለጊዚያዊ ሲቪል አስተዳደር ያስረክቡ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አክለውም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ ፍቃድ ምክር ቤቱን እንዲበትኑና ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
የምክር ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባቀረቡት ጥያቄ፣ “ዜጎች በጠራራ ፀሃይ ይታገታሉ፣ በሚሊዮን ብር ይጠይቅባቸዋል፣ የመንግስት የፀጥታ መዋቅር በተለይም ፖሊስ አማራዎችንና የአማራ ሊሂቃንን የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው እና መንግስትን በተለያየ መንገድ በመተቸታቸው ብቻ የፈጠራ ወንጀል እየተሰጣቸው በማንነታቸው በጅምላ ይታሰራሉ፣ በጅምላ ይከሰሳሉ፣ ፍርድ ቤትም ነፃ ናችሁ ሲላቸው ፖሊስ ግለሰቦችን አስሮ ያቆያል” በማለት ገልፀዋል፡፡
ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ተደርጓል፣ ከፊል ኦሮሚያ ክልልም የጦርነት ቀጠና ሆኖ ሰንብቷል ያሉት አባሉ፣ “ትግራይ፣ አማራና አፋር ፋይዳ ባልነበረው የብልፅግና እና የህወሓት የስልጣን ጦርነት ምክንያት ደቋል፡፡ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ አብዛኛው የደቡብ የኢትዮጵያ ክልልም ከሌሎች የተለየ አይደለም” ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ብልፅግና የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት፣ ነጋዴው ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ሰርቶና ነግዶ የሚኖርበት፣ ገበሬው ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ አግኝቶ አርሶ የሚበላበት እንዲሁም ከተሜውን የሚቀልብበት ሁኔታ መፍጠር አልቻለም ሲሉ የተናገሩት ዶ/ር ደሳለኝ “የኢትዮጵያ ህዝብ በረሃብ እየተሰቃየ ነው የኑሮ ውድነቱ ዝብቡ ህይወቱን መግፋት የማይችልበት ላይ ደርሷል፣ ስራ አጥነት ተስፋፍቷል፣ የነገ ተስፋ የሆኑ ወጣቶጭም አገራቸው ውስጥ ተስፋ በማጣቸው ስደትን ብቸኛ ምርጫ አድርገውታል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በማህበራዊ ዘርፉም ቢሆን ወንጀል በመራከቱን ያነሱት አባሉ፣ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ቤታቸው ፈርሶ ጎዳና ላይ ወድቀዋል ብለዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችም በሰሜኑና በምዕራቡ አገራችን ክፍሎች በነበረው ጦርነትና የምንነት ጥቃቶች የውስጥ ተፈናቃይ ሆነው የሰቆቃ ኖሮ እየገፉ ነው እንዲሁም ባለፉት አምስት አመታት በሚሊጶን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን ተነጥቀዋል ብለዋል፡፡
ጥያቄያቸውን ሲያገባድዱም ለዚህ ሁሎ ቀውስ ተጠያቂው በልፀግና መራሹ መንግስትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወደቀ አመራር ነው ሲል ገልፀው፣ ለወደቀው የእርሶና የብልፅግና አመራር መፍትሄው ምንድነው? የአገራዊ መፍትሄ አፈላላጊ ጉባዔ እንዲዘጋጅ አድርገው ሳረፍድ ለአገራዊ ቀውሱ መላ ቢበጅ አይሻልም ወይ? ለጥቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ይህን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፣ “ከለውጡ በኋላ ፈተና በዝቷል ለተባለው እውነት ነው ፈተና በስቷል ግን ደግሞ ተፈናው እያዳከመን ሳይሆን እንደ ወርቅ አጠንክሮ እያወጣን ነው” ብለዋል፡፡ የችግሩ መንስዔ ፖለቲካዊም ኢኮኖሚያዊም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ፖለቲካዊው ፅንፍ የያዘ ፖለቲካ ነው “ እኔ ብቻ ነኝ የምመራው፣ እኔ ካልመራው ምርጫ ይፍረስ፣ እኔ ካልመራው ፓርላማው ይበተን” የሚል ፅንፍ የወጣ አስተሳሰብ ነው ብለዋል፡፡ ሌላኛው ደግሞ የወል እውነት ማጣት ነው የራስን ሰፈር እውነት የኢትዮጵያ እውነት አድርጎ መሳል ነው ይህ አደገኛ ነገር ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ ተብሎ አቅዶ፣ አስቦ፣ ተዘጋጅቶ፣ ገንዘብ አዋጥቶ፣ ሚዲያ አዋቅሮ መረበሽ አለ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የኢኮኖሚያዊው ችግር ደግሞ ማፈን መቀማት የስራ መስክ መሆኑ ነው ያሉት ዶ/ር አብይ ሽፍቶችን በተመለከት ለህዝባቸው ጥቅም፣ ነፃነት፣ ለተሸነ ነገር እንደሚታገሉ ይናገራሉ ነገር ግን ያን ህዝብ መልስው ያፍናሉ፣ ይይዛሉ ይገድላሉ፣ ህዝብ የሚዘርፍና የሚገድል ሽፍታ የህዝብ ነፃ አውጭ ሊሆን አይችልም ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” እንደተባለው የህወሓት እና የብልፅግና ችግር ከነበረ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የት ነበራችሁ ? ፣ ለምን አታስታርቁም ነበር የሚል ጥያቄም ይነሳል፤ አስታራቂ ሲጠፋ ነው ግጭት የሚበዛው ” ብለዋል። ጠቅይላይ ሚኒስትሩ ” ግጭቱን ማንም ይጀምረው ማንም ጥሩ አይደለም፤ ጥፋት ነው ” ብሎ መቀበል ይገባል ብለዋል።
የትግራይን ህዝብ ከእኛ ጋር ኑር ስንለው መብቱንም በማክበር መሆን አለበት ያሉት ጠቅላይ ምኒስትሩ ይህን ደግሞ ቀዳሚ ተናጋሪ መሆን ያለብን አንድ መሆን አለብን የምንል ሰዎች ነን ብለዋል፡፡
ላለፉት 30 ዓመት በትግራይ እና በአማራ ክልል መካከል የይገባኛል ጥያቄ የሚነሱባቸውን አካባባዎች በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱ ህዝቦች በሰከነ መንገድ እንዲያዩት መክረዋል፡፡ በመሬት ምክኒያት መባላት መገዳደል አያስፈልግም ያሉት አብይ አህመድ በሰከነ መንገድ በመነጋገር ከመፍታት ውጭ ያለው መንገድ ጥሩ አይደለም ሲል አሳስበዋል፡፡
የተፈናቃሉ ዜጎችን በተመለከተ ከኦሮሚያ፣ ከአማራ እንዲሁም ከሌሎች አካባቢ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ አካባቢዎቻቸው መመለስ አለባቸው፣ ኢትዮጵያዊን መሸከም የማይችል የኢትዮጵያ ግዛት መኖር የለበትም ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ቀጥለውም ተፈናቃይን አንቆ በመያዝ የሚነግድ መኖሩን እና ሰው ሲፈናቀል የሚሰፋለት የሚመስለው መኖሩን እንደ ችግር አንስተዋል፡፡ ተፈናቃዮችን መመለስ የሁላችንም ስራ መሆን እነዳለበትም አሳስበው የኦሮሞና አማራ ፖለቲከኞች እንጂ የሁለቱ ክልል ህዝቦች አብሮ የመኖር ችግር የለባቸውም ያሉት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክልሎቹ በትኩረት ሰጥተው በፈጠነ መንገድ አብሮ መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡
ህገ ወጥ ቤቶችን ማፍረስ በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ የሸገር ከተማ ጉዳይ መሆኑንና እና ከዛም ካለፈ የኦሮሚያ ጉዳይ መሆኑን ገልፀው በዛ ደረጅ ነው መስራት ያለበት ብለዋል፡፡ ስራውን በተመለከተ ግን በሁሉም ከተሞች ህገወጥ ግንባታዎች ይፍረሱ የሚል ስምምነት እንዳለ አንስተዋል፡፡ አስ