ዜና፡ በወላይታ የጸጥታ ሃይሎች ታዋቂውን ምሁርና የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አሰፋ ወዳጆን በቁጥጥር ስር አውለዋል

የቀድሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ወዳጆ ምስል የግል ፌስቡክ ገፅ


አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 3/ 2014 ዓ.ም፡- በደቡብ ክልል የወላይታ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው በሶዶ ከተማ የጸጥታ ሃይሎች የወላይታን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ደጋፊ እና የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ  የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ አሰፋ ወዳጆ በድጋሚ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፓርቲው እና ባለቤታቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩት አቶ አሰፋ እሁድ ነሐሴ 1 ቀን በጸጥታ ሃይሎች መታሰራቸውን ባለቤታቸው ምንትዋብ ገብረስላሴ ተናግረዋል። መኖሪያ ቤታቸውም እንደተፈተሸ አክላ ተናግራለች። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አቶ አሰፋ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ እና የታሰሩበትም ምክንያት አልመታወቁን ገልፃለች።

የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ አማኑኤል ሞጊሶ በበኩላቸው ፓርቲው አሰፋ ለምን እንደታሰረ እንደማያውቅ ገልጸው፣ ምናልባት ለወላይታ ዞን  የክልል አደረጃጀት ጥያቄ ካደረገው ግልጽ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

አዲስ ስታንዳርድ በሶዶ ከተማ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እየተነገረ ያለው ተቃውሞ እና ተጨማሪ የጸጥታ ችግር እንዳለ ሊቀመንበሩን ጠይቋል። ነገር ግን ሊቀመንበሩ “ይህ ሀሰት ነው” ሲል ገልፆ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በአዲስ መልክ ለማዋቀር ከታቀደው ጋር በተያያዘ በዞኑ ቅዳሜ ህዝባዊ ሰልፎች ተካሂደዋል የሚለውን አስተባብሏል። የወላይታ ዞን ምክር ቤት ከጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞን  እንዲሁም አምስት ልዩ ወረዳዎች ማለትም አሌ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ ልዩ ወረዳዎች ጋር በመሆን  ባለፈው ሳምንት  በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት  አፈ-ጉባዔ ያቀረቡትን ጥያቄ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ካፀደቀ አንድ ክልል ይመሰርታሉ ተብለው ከሚጠበቁት ዞኖች አንዱ ነው።

አሳፋ ወዳጆ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለወራት በእስር ካሳለፉት ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው።

የወላይታ ዞን ም/ቤት ያቀረበውን የክልል ጥያቄ ተከትሎ  ዞኑ  በፀጥታ ሃይሎች እና በሰላማዊ ሰዎች መካከል የማያቋርጥ የውጥረት ማዕከል ሆናለች። የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ሲቪል ሰርቫንቶች እና አክቲቪስቶች ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በፖሊስ ሲታሰሩ እና ሲፈቱ ቆይተዋል።

በቅርቡ አዲስ ስታንዳርድ በወላይታ በክልል የመደራጀት  እና በዞኑ ስላለው ቀጣይ የፖለቲካ አቅጣጫ. በሚል ርዕስ ተከታታይ ትንታኔዎችን ማቅረቡ ይታወቃል። አስ  

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.