ዜና፡ በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በታጠቁ ቡድኖች ከ100 በላይ ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለፀ፣ መንግሥት የሲቪሎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ አሳሰበ

ኡሙሩ ወረዳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ከ100 በላይ ሲቪል ሰዎች በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ)፣ በአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎች እና በግለሰቦች መገደላቸውን ገልፆ መንግሥት የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል ሲል አሳሰበ፡፡

ኮሚሽኑ ይህን ያለው ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ሲሆን ጥቃጡ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በኡሙሩ፣ በሆሮ ቡልቅ እና በጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች መፈፀሙን አስረድቷል፡፡

ኢሰመኮ በካባቢዎቹ ከነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ)፣ በአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎች እና ግለሰቦች በተከታታይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ100 በላይ ሲቪል ሰዎች የተገደሉ መሆኑን የገለፀ ሲሆን አክሎም የግል ንብረት እና የቁም ከብቶች መዘረፋቸውን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ያለበቂ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን ኮሚሽኑ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከአካባቢው የፍትሕና የአስተዳደር አካላት እንዲሁም በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የእርዳታ ድርጅቶች ያሰባሰባቸው መረጃዎች እና ማስረጃዎች ያሳያሉ ሲል ገልጿ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት በአካባቢው ብሔርን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃ ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በማሳደግ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል” ሲሉ በድጋሚ አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰን ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተጨማሪ የጸጥታ ሥጋቶች በመኖራቸው በታጠቁ ቡድኖች በሲቪል ሰዎች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ተጨማሪ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት እንዲሠራ ማሳሰቡን አስታውሶ፤ በአካባቢው ሲቪል ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች አሁንም ተሰፋፍተው መቀጠላቸው እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.