በአዲስ ስታንዳርድ ሪፖርተሮች
አዲስ አበባ፣መስከረም 26/2015 ዓ.ም፡- ጦርነትን በመሸሽ ከትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልል ለቀው የሚሰደዱ ሴቶች እና ልጃገረዶች ለጠለፋ እና ለፆታዊ ጥቃት ንግድ ተጋላጭነታቸው እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሙያዎች አስታወቁ።
“በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልል ሴቶች እና ልጃገረግ ተፈናቃዮች ወደ ተሻለ ስፍራ ለመሄድ ሲሞክሩ እየተጠለፉ መሆናቸው አሳስቦናል” ብለዋል ባለሙያዎቹ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባወጣውመግለጫ “ባለሞያዎቹ በተለይም ወሲባዊ ባርነትን ጨምሮ ለፆታዊ ጥቃት የሚደረግ ዝውውር አደጋ” እንዳሳሰባቸው ገልጿል፡፡
ሁሉም ተፋላሚ ኣካላት ከዚህ ቀደም አስገድዶ መድፈርን እና ጾታዊ ጥቃትን እንደ ጦርነት መሳሪያ ይጠቀማሉ በማለት በመብት ተሟጋቾች መከሰሳቸው ይታወሳል።
በትግራይ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ ከቤተሰቦቻቸው የተነጠሉ ህጻናት ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸውን የገለፁት ባለሙያዎቹ፣ አሁንም በክልሉ ያለው የሰብዓዊ አገልግሎት እጥረት ችግሩን አባብሶታል ብለዋል።
ባለሙያዎቹ “ጠለፋ እና መፈናቀልን ተከትሎ በሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ለጾታዊ ጥቃት ተጋለጭ ለሆኑት ኤርትራዊያን ሴቶች እና ልጃገረዶች” ስጋታቸውን አንስተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ ባለሙያዎቹ ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ መንግስታት ጋር ምክክር ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጾ የሴቶችና ልጃገረዶችን ለፆታዊ ጥቃት የሚደረጉ ዝውውሮችን ለመከላከል በአስቸኳይ ሀገራዊ፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን እርምጃዎችን እንዲወሰዱ አሳስቧል። አስ