ዜና፡ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሶስት የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች በትምህርት ስርዓት ውስጥ ይበልጥ ለማጠናከር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ መጋቢት 14/2014 –  በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአፍ መፍቻ ቋንቋነት እየተጠቀሙባቸው ባሉት ሶስት ቋንቋዎች ስርአተ ትምህርቱን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኮሞ፣ ማኦ እና ጉዋማ ቋንቋዎችን በትምህርት ስርዓቱ ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ የክልሉ ትምህርት ቢሮ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ባደረጉት የምክክር መድረክ ጉዳዩ ይፋ የተደረገው። የውይይቱ ተሳታፊዎችም ለእነዚህ ቋንቋዎች እድገት ማነቆ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢንያም መንገሻ እንደገለፁት በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሶስቱን ቋንቋዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋነት በማስተማር ላይ መሆናቸውን ገልፀው የቋንቋ ስልቶችን በመተግበር የሚሰራ አደረጃጀት በማጎልበት ጥረቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የመምህራንን ደመወዝ ማሻሻል እና አቅማቸውን ማሳደግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። 

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው፥ ቋንቋዎችን በመማር ማስተማር ሂደት ውጤታማ ለማድረግ የክልሉ መንግስት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ነገር ግን የመምህራን እጥረት፣ የክትትልና ድጋፍ ውስንነት፣ የመማሪያ መጽሀፍትን በወቅቱ ማድረስ እና በተማሪዎች ማንበብና መጻፍ ላይ ያሉ ክፍተቶች እንደ ተግዳሮቶች ጠቁመዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ የስራ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.