ዜና፡ በሸዋሮቢት ከተማ የፖሊስ አባል ተደገለ፤ ግድያው በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ የተገደሉ የአካባቢ ባላስልጣንና የፀጥታ አካልን ብዛት ወደ አራት ከፍ አድርጎታል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30 / 2015 ዓ.ም፡- ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ ትላነት ሰኔ 29 ቀን  ማታ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር 08 ቀበሌ ከምሽቱ 4 ስዓት በስራ ላይ እያሉ ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

የአሁኑ ግድያ በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ የተገደሉ የአካባቢ ባላስልጣንና የፀጥታ አካልን  ብዛት ወደ አራት ከፍ አድርጎታል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮኖት ከተማ ማክሰኞ ሰኔ 27 የከተማ አስተዳደሩ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች ተገድለዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ  የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና  የወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ም/ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ወርቁ ሽመልስ ለስራ በወጡበት ለጊዜው ማንነቱ ባልታወቀ አካል በተከፈተባቸው ጥቃት ህይወታቸው ያለፈው በዚሁ ሳምንት ነው።

የሸዋሮኖት ከተማ አስተዳደሩ ባወጣው መግለጫ የምክትል ሳጅንን ነፍስ በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን እየተመኘን ፤ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ደግሞ ለቤተሰቡ መጽናናትን እንዲሰጥ ተመኝቷል፡፡

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ማክሰኞ ሰኔ 27 ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች መገደላቸውን ተከትሎ የከተማ አስታዳደሩ ኮማንድ ፖስት  በከተማዋ ከሰኔ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ  ከምሽቱ 12 ስዓት ጀምሮ ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ተገድቦ በትግራ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

በተጨማሪም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የምሽት ክለቦችን ጨምሮ ከምሽቱ 12 ስዓት  በኃላ  ምንም አይነት አገልግሎት አንዳይሰጡ ክልከላ አድርጓል። እንዲሁም የከተማው ነዋሪ ለጸጥታ መዋቅሩ እገዛውንና ድጋፍ በማድረግ ከተማዋን ካለባት ከፍተኛ የጸጥታ ችግር  ልንታደጋት ይገባል ሲል ዛሬ ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።

የጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፓስት በከተማዋና በአካባቢዉ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እንዲሆን እና  ዜጎች ያለ ስጋት ወጥተው የሚገቡበት ለማድረግ ብዙ ጥረት የተደረገ ቢሆንም አሁንም ከተማዋን ሰው አልባ እንድትሆንና ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዲከሰት ጥረቶች እየተደረጉ በመሆኑ ክልከላዎች መደረጉ አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.