ዜና፡ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሁለት ወረዳዎች በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ከባድ ዝናብ በሰብልና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ

በብሩክ አለሙ

አዲስ አበባ: ሰኔ 8/ 2014 ዓ.ም ፦በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በሰሜን ሜጫ ወረዳ ቆለላ ቀበሌ  ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ.ም.  በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት ከ 1000 በላይ የአርሶአደር መኖሪያ ቤቶች ላይ  ሙሉ በሙሉ ውደሙት ማድረሱና  ከባድና ቀላል የንብረት ጉዳት መድረሱን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን  አስታውቀ።

በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ጎጃም ዞን በሰከላ ወረዳ ከፍተኛ በረዶ ቀላቀሎ የጣለው ዝናብ በሰብል ምርት እና በአርሶ አደሮች መኖሪያ ቤት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የሰከላ ወረዳ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል፡፡

የሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን እንደገለጸው በቆላላ ቀበሌ ጋፈራ ፣ አቪዛርታ፣ ባስሊ፣ ታች ቆለላ እና ደብር መንደር በተባሉ ጎጦች 1409 የሚደርሱ የአርሶአደር መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ውደሙት ደርሷል። 

የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሴ አቤ እንዳሉት ከሆነ ከቀኑ 9:00-12:00  በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ከላይ በተጠቀሱት ጎጦች በሚኖሩ አባወራዎች ላይ አደጋው ሊደርስ ችሏል።

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰው ላይ ጉዳት ባይደርስም  የ1,409 የአርሶአደር መኖሪያ ቤቶች ውድመት፣ የ144 እንስሳት ሞት፣ በአትክልት እንዲሁም በሰብል ላይ ውድመት ማድረሱን ከሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በተጨማሪም ፣ ለዘር የተዘጋጀ 1,500 ማዳበሪያ፣ 11,200 ኩንታል የተቀመጠ እህል እና 45 ኩንታል ምርጥ ዘር መበላሸቱም ተገልፀል፡፡

ጉዳት ለደረሰባቸው ሰውችም አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረግ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው በጣለው ዝናብ በመኖሪያ ቤት፣በእንስሳት እና አትክልትና ፍራፍሬ ጉዳት መድረሱን ካረጋገጠ በኋላ እንደየጉዳት መጠናቸው በየቀበሌዎች የሚያስፈልጉ አስቸኳይ ድጋፎች እንዲደረጉ የተዋቀረው ኮሚቴ ለሚመለከተው የዞን አመራር አውቅና መፍጠሩን አስታውቋል።

አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረግ የተዋቀረው ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ኤልያስ አሳየ ውይይት በማድረግ ድጋፍ እንዲደረግ በአደጋው የደረሱትን ችግሮች ለይተው ለሚመለከተው አካል አስተላልፈናል ብለዋል።

በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ጎጃም ዞን በሰከላ ወረዳ ግንቦት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9 ስዓት ጀምሮ ያለማቋረጥ ከሁለት ሰዓት በላይ በጣለው ከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ቀበሌዎች መካከል በባህር ዛፋ፤ በጅግሪታ በአምቢሲና በአባይ ቀበሌዎች ጉዳት አድርሷል፡፡ ዝናቡም የድንች ሰብልን  ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን በባህር ዛፋ ቀበሌ በአርሶ አደሮች የመኖሪያ ቤት ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተወጣጣው የአመዝኮ ቴክኒክ ኮሚቴ ቡድን የተጎጅ አርሶ አደሮችን ሰብልና መኖሪያ ቤት የጎበኘ ሲሆን  የጉዳቱ ሰለባ የሆኑት አርሶ አረዶች ለኮሚቴው  እንደተናገሩት  በዘነበው ዝናብ የድንች፣ የገብስ፤ በመስኖ የለማና ባልደረሰ በቆሎ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረስም አልፎ የመኖሪያ ቤት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሰ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

የቀበሌው የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ሙሉነህ አይቸው ዝናቡ የድንች ሰብልን መቶ በመቶ ማውደሙንና የአርሶ አደሮችን የቆርቆሮ መኖሪያ ቤት በመበጣጠስ የእለት መጠለያቸው ዝናብ ለመከላከል እስከሚያስቸግር ድረስ ጉዳት ያደረሰ መሆኑንና በበጋ ወቅት ያመረቱትን የጤፍ፣ የበቆሎ፣ የአተርና ባቄላ ምርቶች ማሳቸው ላይ ሳያነሱ ውሃ በመሙላቱ ለከፍተኛ ጉዳት ስለዳረገ መንግስት በችግሩ ልክ ለአርሶ አደሮች ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የወረዳው ግብርና ፅህፈት ቤት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ቡድን መሪ አቶ በለጠ ወርቄ በሰጡት ማብራሪያ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ በባህር ዛፋ፤ በአምቢሲ ፣ በጅግሪታና በአባይ ቀበሌወች ላይ ተመሳሳይ ጉዳት ያደረሰ መሆኑን ገልጸው ዞኑ ከክልሉ ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ድጋፍ የሚገኝ ከሆነ ከማህበረሰቡ ውስጥ አቅም የሌላቸው ተጎጅ የህብረተሰብ ክፍሎች ተለይተው ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡በተጨማሪም አቶ በለጠ የቴክኒክ አመዝኮ ኮሚቴ ችግሩን ለማሳየት በጣረው ልክ የወረዳው አብይ ኮሚቴም አስፈላጊውን ውሳኔ እንዲሰጡ አሳስበዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.