አዲስ አበባ ሚያዚያ 5/2014፡ ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ድንበር በኩል ከሀገር ሊወጡ የሞከሩ ከ90 በላይ ስደተኞችን በአካባቢው ፖሊስ መያዘቸውን የባቲ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አፋር ክልል አጎራባች የሆነችው ባቲ ወረዳ በጅቡቲ አቋርጠው ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለመውጣት ለሚፈልጉ ህገወጥ ስደተኞች ተመራጭ መሻገሪያ ሆናለች።
የባቲ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ሊያቋረጡ የነበሩ 22 ሰዎች፣ 10 ወንድ እና 12 ሴቶችን የጫነ ተሸከርካሪ ኬላ ጥሶ ሊያልፍ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዘገበው መጋቢት 29 ቀን ነበር። ከአማራ ክልል ከደቡብ ወሎ፣ ከሸዋ ሮቢት እና ከቦረና ወረዳዎች የመጡ ተጓዦቹ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የተሰባሰቡ መሆናቸውን የአካባቢው ፖሊስ ገልጿል።
በተመሳሳይ መልኩ ቅዳሜ ሚያዚያ 1ቀን በህገ ወጥ መንገድ በኤፍኤስአር መኪና ድንበር ለማቋረጥ ሲሞክሩ የነበሩ 74 ሰዎች መከላከያ ሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ይህ ሁለተኛው ቡድን 50 ወንዶች እና 24 ሴቶች ስደተኞች ነበሩት ሲል ቢሮው ገልጿል።
ይህ የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት በሳውዲ አረቢያ ውስጥ በእስር ቤቶች እና በእስር ቤቶች ውስጥ የሚማቅቁ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደ አገራቸው መመለስ በጀመረበት ወቅት ነው። በሳወዲ በማቆያ ጣቢያዎች እና እስር ቤቶች ውስጥ ከ100,000 በላይ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ እንደሚገኙ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከዚህ ቀደም በወጡ ዘገባ ላይ እንደተገለጸው የሳዑዲ መንግስት ህጋዊ እውቅና ያላቸውን ሰዎች ላይ ጭምር ርምጃ መወሰዱ ይታወሳል።
በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ወሎ ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው አካባቢው በጅቡቲ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለሚጓዙ ስደተኞች መነሻ ከሚባሉት ዋና ቦታዎች አንዱ ሆኗል። ከዚህ ቀደም ስደተኞቹ ከገጠር ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ሲሆን ጉዞ የሚጀመሩት አሁን ላይ ግን እንደ ወሎ ካሉ ገጠር በቀጥታ ወደ ውጭ ሀግር መሰደድ ጀምረዋል።
ለበለጠ መረጃ የባቲ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ እና ፖሊስን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።አስ