ዜና፡ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ ቀን ቆረጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ


ዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2/2014 ዓ.ም፡- በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለማድረግ ማቀዱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
በዚህም መሰረት የደራሼ፣ የአማሮ፣ የቡርጂ፣ የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች እንዲሁም የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የደቡብ ኦሞ፣ የጌዴኦ፣ የኮንሶ ዞኖች ሕዝበ ውሳኔው ተፈጻሚ እንደሚሆንም ተጠቁሟል።

ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሚገኙ የ6 ዞኖች (የጋሞ፣ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ኮንሶ እና የደቡብ ኦሞ ዞኖች) እና የ5 ልዩ ወረዳዎች(የቡርጂ፣ የአማሮ፣ የደራሼ፣ የባስኬቶ እና የአሌ ) በአንድ ክልል የእንደራጅ አቤቱታን ተቀብሎ ከመረመረ በኃላ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ ማስተላለፉ  ይታወሳል፡፡

ምክር ቤቱ የጋራ ክልል የመመስረት ጥያቄው ከሕገ መንግሥቱ አንፃር ውሳኔ ለመስጠት እንዲያስችል የሕዝብን ይሁንታ ማረጋገጥ ስለሚያስፈልግ ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ በሆነ መልኩ ገለልተኛ በሆነው ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አማካኝነት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅና የሕዝብ ውሳኔው ውጤት ሪፖርት ለምክር ቤት እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል የሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው ቦርዱ ሕግና አሰራርን ተከትሎ እንዲከናወን የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም ገልፀዋል።

ሕዝበ ውሳኔውም በሕግ አግባብ ደረጃውን በጠበቀና እውነተኛነቱን ባረጋገጠ መልኩ የሕዝብን ሃሳብ በመለካት ለማሳወቅ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የህዝበ ውሳኔ ዕቅድ ባቀረቡበት ወቅት ለህዝበ ውሳኔው 18 ሺህ 885 ሰዎች በአስፈፃሚነት እንደሚሰማሩ የገለፁት የቦርዱ የኦፕሬሽን አማካሪ አቶ ብሩክ ወንድወሰን አርባ ምንጭ ከተማ የህዝበ ውሳኔው ማስተባበሪያ ማዕከል እንደምትሆን ገልፀው የህዝበ ውሳኔ ድምጽ ውጤት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.