አዲስ አበባ፣ ህዳር 10/2015 ዓ.ም: – የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈው ወር የውጭ ምንዛሪ እንዳይሰጣቸው ከታገዱት 38 ዓይነት የሸቀጦች ምድብ በከፊል ማስተካከያ ማድረጉን አስታወቀ።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት ነፃ የተደረገው ምርትና አገልግሎታቸውን በውጭ ምንዛሪ ለመሸጥ ፍቃድ የተሰጣቸው ሆቴሎች፣ የቤት እቃዎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ሱፐርማርኬቶች እና ከቀረጥ ነፃ የሆኑ ሱቆች ናቸው።
የማሻሻያው ተጠቃሚዎቹ እቃዎቹን የራሳቸውን የውጭ ምንዛሪ ተጠቅመው እንዲያስገቡ ፈቃድ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የገንዘብ ሚኒስቴር ማሻሻያውን ተከትሎ እንዲያስፈፅሙ ለብሔራዊ ባንክ እና ለጉምሩክ ኮሚሽን ደብዳቤ ልኳል።
በደብዳቤው መሰረት መንግስት በራሳቸው ገበያ የውጭ ምንዛሪ የሚያመነጩ የራሳቸው የውጭ ምንዛሪ ተጠቅመው እንዲያስገቡ ነው ማሻሻያውገ ያደረገው።
በደብዳቤው ከአንድ ወር በፊት መንግስት ከላይ የተጠቀሱትን ምርቶች ጨምሮ በ38 ምድቦች ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ሸቀጦች የውጭ ምንዛሪ መከልከሉን አስታውቆ ነበር ይሁን እንጂ በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ ሸቀⶏችን የማስገባት ፈቃድ ላላቸው ማሻሻያ መደረጉን አትቷል።
‘’አሁን የተደረገው ማሻሻያ ምርቶቻቸውን እና አገልግሎቶቻቸውን በውጭ ምንዛሪ ለመሸጥ፣ የራሳቸውን የውጭ ምንዛሪ ተጠቅመው እቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ፍቃድ ላላቸውን ብቻ የሚመለከት ነው” ሲልም አስገንዝቧል።
መንግስት በጥቅምት 2022 ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት የማይፈቀድላቸው በ38 ዓይነት ምድብ የተዘረዘሩ እቃዎች ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
እንደ የመንግስት ባለስልጣናት ገለጻ እርምጃው የተወሰደው ለአስፈላጊ ዕቃዎች ቅድሚያ ለመስጠት ነው።
መንስግስት ከውጭ ይገቡ ለነበሩ 38 ምርቶች የውጭ ምንዛሪ እንዳያገኙ ላልተወሰነ ግዜ የጣለውን እገዳ ተከትሎ የዕለት ተለት ኑሯቸው ከምርቶቹ ጋር ተያያዠነት የነበራቸው ነጋዴዎች ላይ ጫና እያሳደረባቸው መምጣቱን በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎች መናገራቸዉን አዲስ ስታንዳርድ ዘግባ ነበር፡፡አስ