ዜና፡ ሉሲ ቀጥ ብላ ትራመድ እንደነበር ሳይንሳዊ ጥናት አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7/2015 ዓ.ም፡- የካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ሳይንቲስቶች በሉሲ ቅሪተ አካል ላይ ያካሄዱት ጥናት እንደሚያመላክተው ሉሲ መገጣጠሚያ ጉልበት እንደነበራት እና ይህም ቀጥ ብላ እንድትራመድ እንዳስቻላት ጠቁሟል። በ1967 ዓ.ም በኢትዮጵያ አፋር አካባቢ የተገኘችው እና በወቅቱ ሉሲ የሚል መጠሪያ የተሰጣት ቅሪት አካል ከሶስት ነጥብ ሁለት ሚሊየን አመት በፊት ትኖር እንደነበር መገለጹ ይታወሳል።

በሮያል ሶሳይቲ ኦፕን ሳይንስ ጆርናል ላይ የወጣው ጥናት እንደሚያሳየው የጉልበት መገጣጠሚያ ስለነበራት ልክ እንደ አሁኑ የሰው ልጅ አረማመድ ቀጥ ብላ ለመራመድ እንዳስቻላት አመላክቷል። ወደ ዛፍ በቀላሉ ለመንጠላጠል እና ለመውጣት አስችሏታልም ተብሏል።

ቁመቷ አንድ ሜትር ከአስር ሴንቲ ሜትር እንደነበር የጠቆመው ጥናቱ 27 ኪሎ ትመዝን ነበር ተብሏል። የሉሲ እድሜም በሃያዎቹ ውስጥ መሆኑን የጥርሱ አበቃቀልን ተገን ተደርጎ መገመቱን ጥናቱን ተከትሎ የወጡ ዘገባዎች አመላከተዋል። ጥናቱን የመሩት የካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሩ አሽሌይህ ዋይስማን መሆናቸው ተገልጿል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.