ዜና፡ቢያንስ 12ሺ የሚሆኑ አዲስ ተፈናቃዮች በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ተጠልለዋል፤አብዛኞቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት

የመርሳ ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን ማህበረ በኩር ሰንበት ት/ቤት መርሳ ከተማ በመጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብ የምግብ እርዳታ ሲሰጡ። ፎቶ: መርሳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

አዲስአበባ፣መስከረም12/2014 ዓ.ም፡- በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ባወጣው ሪፖርት መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ በያንስ 12,000 የሚሆኑ አዲስ ተፈናቃዮች ተጠልለው ይገኛሉ። ሪፖርቱ ከተፈናቀሉት መካከል ብዙዎቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ሲል አክሎ ገልጿል።

በሪፖርቱ መሰረት በሰሜኑ የሃገሪቷ ክፍል እየተደረገ ያለው ጦርነት በሰሜን ጎንደር፤ ሰሜን ወሎ እንዲሁም ዋግ ኽምራ አከባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እየጎዳ  ነው፡፡ በሰሜን ጎንደር ደባርቅ፣ በሰሜን ወሎ ቆቦና ወልድያ እንዲሁም በዋግ ኽምራ አበርገሌና ሰቆጣ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ምክንያት የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች ወደ አከባቢዎቹ ለመድረስ  አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል፡፡ ንብረትና የሲቪል መሰረተ ልማቶችም መውደማቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በሰሜን ወሎ ዞን ጃራ የስደተኞች መጠለያ  መዘረፉ እና አንዳንድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳትና ውድመት መድረሱን ሪፖረቱ ይፋ አድርጓል።

በከባቢው ተጠልለው የነበሩ ከ30ሺ ባላይ ተፈናቃዮች ከጃራ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ወልደያ አቅራብያ ግጭት መቀስቀሱን የሚያወሱ ዜና መሰራጨቱን ተከትሎ ስድተኞቹ ለድህንነታቸው በመስጋት ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ከመጠልያው ለቀው ወጥተዋል።

ባሁኑ ወቅትም አብዛኞቹ ተፈናቃዮች የመንግስትና የሰብአዊ አጋር ተቋማት ምግብ እና ውሃ የማጓጓዝ አገልግሎት መስጠት ወደ ጀመሩበትና ወደ ወደመው ስፍራ ተመልሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ የነዳጅ እጥረት እና የተቆራረጡ እርዳታ ተግዳሮቶች እየተደረገ ያለውን ጥረቶችን እየገደበ ነው።

የክልሉ ባለስልጣናት ቁጥራቸው እያሻቀበ የመጣውን ተፈናቃዮችን ለማስተናገድ ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰሜን ወሎ ዞን በመርሳ ከተማ ስድስት የጋራ መጠለያዎችን አቋቁመዋል። ከ12,000 ያላነሱ አዲስ ተፈናቃዮች በከተማዋ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው። በመርሳ በኢንተር ኤጀንሲ ፍላጎት ግምገማ ተልአኮ የተገኘውን ውጤት ተከትሎ አጋር ድርጅቶች እነሱን ለመርዳት ምግብና ምግብ ነክ ያለሆነ ቁሳቁሶችን ለሰራጨት በማሰባሰብ ላይ ሲሆኑ ተንቀሳቃሽ የጤና እና የስነ ምግብ ቡድን ግን ቀደም ብሎ ወደ ከተማዋ ተልከዋል።

በአማራ ክልል አጠቃላይ የምግብ ዋስትና ደረጃ አሳሳቢ ነው ያለው ሪፖርቱ ቢያንስ 5 ሚሊዮን ህዝብ ለምግብ እጦት ተጋልጧል ብሏል። በተለይ ግጭት በተከሰተባቸው የክልሉ አካባቢዎች ሁኔታው የከፋ ሲሆን ከእነዚህ አካባቢዎች 80 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አለ፡፡

በወረሃ መጋቢት 2014 ዓ.ም. የታተመው የቅርብ ጊዜ የመንግስት የተመጣጠነ ምግብ አደጋ የተጋረጠባቸው አካባቢዎች ምደባ፤ በክልሉ ውስጥ 125  ወረዳዎች የተጎዱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 74ቱ ቅድሚያ ምላሽ(እርዳታ) የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ይፋ አድርጓል። ብርድ ልብስ እና የታለመ ተጨማሪ ምግብ እንዲሁም የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብሮች በመካሄድ ላይ ናቸው፣ ነገር ግን በሀብቶች ውስንነቶች ምክንያት አጋሮች ያልተሟላ ምግብ (በስንዴ ብቻ የተገደበ) የሚያገኙትን ጨምሮ የምግብ ዋስትና ከሌላቸውን ሰዎች ውስጥ 83 በመቶውን ብቻ ተደራሽ ያደርጋሉ።

በሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖችን ጨምሮ በርካታ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ መከሰቱንም ተገልጿል። በክልሉ የጎርፍ አደጋ መከላከል እቅድ መሰረት ከ487,000 በላይ ሰዎች ሊጎዱ እንደሚችሉ የጠቆመ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ከ29,000 በላይ የሚሆኑት በሰባት ዞኖች በሚገኙ 32 ወረዳዎች ሊፈናቀሉ ይችላሉ ብሏል። የምግብ ዕርዳታ አሁንም እየተሰጠ ቢሆንም በሃብት እጥረት ምክንያት እጅግ በጣም ውስን ነው።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.