አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8/2014 ዓም – በደሴ ከተማ አስተዳደር በቧንቧውሀ ክፍለ ከተማ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ በነፍስ ማጥፋት ተፈላጊ የነበሩ ግለሰቦች በምርመራ ክፍል ውስጥ በጣሉት ቦንብ የ5 ሰዎች ሂወት ትናንትና ማለፉን የከተማው አስተዳደር ኮሚኒከሽን ጉዳዮች ቤሮ አስታወቀ።
መነሻቸውን ከደሴ ዙሪያ ወረዳ “ፅድ ገበያ” አካባቢ ያደረጉ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ የ25 ዓምት ፍርድ የተፈረደባቸው 4 ተጠርጣሪዎች ወደ ደሴ ከተማ አስተዳደር በመግባት የተለያዩ ጥፋቶችን ለመሰንዘር አቅደው እንደገቡ መግለጫው ጠቅሶ በደሴ ከተማ አስተዳደር እና በደቡብ ወሎ ፓሊስ ጥመረት በትላንትናው እለት ከቀኑ 10:00 አካባቢ ተጠርጣሪዎቹ እንደተያዙ እና ወደ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ ለምርመራ እንዲገቡ አስታውቋል ።
መግለጫው አክሎም በወንጀል ሲፈለጉ የነበሩትን 4 “ሽፍቶች” የያዙትን ትጥቅ እንዲፈቱ ከፓሊስ የተሰጣቸውን መመሪያ ባለመቀበል እና መመሪያውን በመተላለፍ የታጠቁትን ቦንብ አውጥተው በማፈንዳት ተፈላጊ ሽፍቶቹን ጨምሮ አንድ መደበኛ ፓሊስ እና ልዩ ሀይል በጥቅሉ የ5 ሰዎች ሂወት እንዳጠፋ ገልጾ 1 ወንጀለኛ እጁን እንደሰጠ የደሴ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አሳምን ሙላት ለኮሚኒዩኬሽን ቢሮው መናገራቸውን አትቷል ።
አዲስ ስታንዳርድ ወደ ደሴ ከተማ በቧንቧውሀ ክፍለ ከተማ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ ስልክ ደውላ ያነጋገረችው ሰሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ እንዴት ታጥቀው እንደታሰሩ ላቀረበችለት ጥያቄ “ጉዳዩን በማጣራት ላይ በማጣራት ላይ ነን። ሙሉ መረጃ አሁን ላይ መስጠት አላችልም “ብሏል። አስ