አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 ዓም:- በታንዛኒያ እስር ላይ የነበሩ 126 ኢትዮጵያውያን ከእስር ተፈተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ታንዛኒያን አቋርጦ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚደረግ ሕገ ወጥ ጉዞ በርካታ ኢትዮጵያውያን በታንዛኒያ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር እየዋሉ ለእስር እንደሚዳረጉ ይታወቃል።
ከነዚህም መካከል126 ኢትዮጵያውያን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲበአገሪቱ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመቀናጀት ወደ ኢትዮጵያ መሸኘታቸውተገልጿል፡፡
የተቀሩትም በቀጣይ በተቀመጠላቸው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ወደ አገራቸው መመለስ እንዲችሉ እየተሰራ እንደሚገኝ ኤምባሲው አስታውቋል፡፡
በርካታ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በመታለል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከፍለው እጅግ አደገኛ የሆነ ህገ ወጥ ጉዞ የሚያደርጉ ሲሆን÷በመንገዳቸው ላይም ለረሃብ፣ ለእስር፣ ለአስከፊ ስቃይ ብሎም ለሞት እንደሚዳረጉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ አስ