በእቴነሽ አበራ @EteneshAb
ሐምሌ 20፣ 2014 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡ የኢትዮጵያ ደም ባንክ አገልግሎት በክረምቱ ምክንያት የደም ለጋሾች እጥረት እንዳጋጠመው አሳወቀ። የደም ባንኩ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀብታሙ ታዬ ለአዲስ እስታንዳርድ የእጥረቱ ምክንያት የትምህርት ቤቶች በክረምቱ ምክንያት መዘጋጀት መሆኑን ገለፀዎል። ሀላፊው ጨምረው ” አሁን ላይ በቀን ከ250-300 ዩኒት ደም እየሰበሰብን ነው ነገር ግን በቂ አይደለም” ብለዋል።
ሀብታሙ ጨምረው በበጋ ወቅት 400 ዩኒት ደም ይሰበሰብ ነበር ነገር ግን የክረምቱ ትምህርት ቤቶች መዘጋት ቁጥሩን ቀንሶታል። ” የሚሰበሰበው ደም ማነስ ከፍተኛ የሆነ ክፍተት ፈጥሯል። በየቀኑ የሚሰበሰበው ደም በከተማው ውስጥ ለሚገኙ የግል እና የመንግሥት ሆስፒታሎች ሰለሚከፋፈል ከፍ ያለ ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥመን በቂ የሆነ ክምችት የለንም።”
ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በእጥረቱ ከተጎዱት ሆስፒታሎች አንዱ ነው።
በከተማው ውስጥ 11 ጊዜዊ የደም መሰብሰቢያ ጣቢያዎች ስላሉ ደም ለጋሹ ማህበረሰብ ዝናቡን ታግሰው እንዲለገሱ አቶ ሀብታሙ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ የደም ባንክ 43 ቅርንጫፎች ሲኖሩት ሶስቱ ትግራይ ክልል ውስጥ ነው የሚገኙት። አቶ ሀብታሙ እጥረቱ በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልሎችም እንደተከሰተ ጨምረው ነግረውናል። አስ