አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015፦ የአዊ ብሄረሰብ መለያ የሆነውን የአገው ፈረሰኞች በዓል የአዊ ብሄረሰብ መለያ የሆነውን የአገው ፈረሰኞች በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባሕል ድርጅት (UNESCO) በማስመዝገብ የሃገራችን አንዱ ልዩ ገጽታ ማሳያ ለማድረግ እየተሠራ ነው በማለት የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ።
ከአማራ ኮሙኒኬሽን በተገኘው መረጃ መሰረት፣ የአገው ፈረሰኞች በዓል የአዊ ሕዝብ ዘንድ ላለፋት 82 ዓመታት ተከብሯል። ዘንድሮ ለ83ኛ ጊዜ በእንጂባራ ከተማ በድምቀት ይከበራል።
“ፈረሶች ለአገው ሕዝብ ሃገሩን ከጠላት ለመከላከል ለአርበኞች የጀግንነት ክንዶች ናቸው። ለማጓጓዣ፣ ለሰርግ፣ ለሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ ለለቅሶ ስርዓት፣ ለእርሻ አገልግሎት በመስጠትም ከሕዝቡ ጋር የተሳሰረ ቁርኝት አላቸው” በማለት የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አክሎ ገልጧል።
የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ከ 62 ሺ በላይ አባላት ያሉት ሲሆን የአባላቱን ቁጥር 150 ሺ ለማድረስ ታቅዶ እየተሠራ ነው።
ማኅበሩም ከ 52 ሺ በላይ ፈረሶች ያሉት ሲሆን፣ 4 ሺ ፈረሶች በበዓሉ ላይ የተለያዩ ትርኢቶችን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል መረጃው አክሎ ገልጧል። አስ