ዜና፡ ለስምንት ወራት በእስር ላይ ከነበሩ አምስት የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች ሶስቱ ተፈቱ፤ የተከሳሽ ጠበቃ በፍርድ ቤት አሰራር ላይ ቅሬታ አቅርበዋል

በምህረት ገ/ክርስቶስ @MercyG_kirstos

አዲስ አበባ፣ ጥር 9/2015 ዓ/ም፡- መቐለ የሚገኘው ፍርድ ቤት “የጠላትን ፕሮፓጋንዳ አሰራጭተዋል” ተብለው በአካባቢው ባለስልጣናት ከተከሰሱ አምስት የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች መካከል ሦስቱ ከስምንት ወራት የእስር ቆይታ በኋላ እንዲለቀቁ አድርጓል፡፡

ምስጋና ስዩም ባሳለፍነው ሳምንት ከእስር ከተለቀቁት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ሲሆን ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው  ከህዳር 28 እስከ ሰኔ 28 ቀን 2021 የፌዴራል መንግስት መቐለን ጨምሮ የትግራይን ክልል ተቆጣጥሮ በነበረበት ጊዜ በተሸመው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስራ መታዘዛቸውን ገልጧል፡፡

ሰኔ 28 ቀን 2021 ህወሃት መራሹ የትግራይ ክልል አስተዳደር  አብዛኛውን የክልሉን አካባቢዎች ከተቆጣጠረ በኋላ ግንቦት 26፣ 2022 አምስት ጋዜጠኞች እንዲታሰሩ አድርገዋል፤ አንዳንዶቹ በስራ ላይ የነበሩ ሲሆን ገሚሶቹ ደግሞ ከመታሰራቸው በፊት ከስራ የታገዱ ናቸው።

ከአምስቱ ጋዜጠኞች ሁለቱ ማለትም ተሸመ ተማለው እና ምስጋና ስዩም ነፃ የሆኑት ጥር 11 2023 ሲሆን ሶስኛው ማለትም ሃበን ሀለፎም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነው፡፡ ነገር ግን በተመሳሳይ ክስ የተከሰሱት ሀይለሚካኤል ገሰሰ እና ዳዊት መኮንን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

ለ16 አመታት በትግራይ ቴሌቭዥን ሲያገለግል የቆየው ምስጋና ስዩም እንደገለፀው ጋዜጠኞቹ መቀለ ከተማ ሰሜን ከፍለ ከተማ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከስምንት ቀን በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

“ለስምንት ቀናት በእስር ላይ እነድንቆይ ካደረጉን በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበን ፖሊስ ምርመራውን ጀመረ” የሚለው ምስጋና “ምርመራው፣ ክሱ ከመመስረቱ በፊት ለአራት ወራት ያህል ቆይቷል። በኋላ ላይም ተከሰሾቹ ክሱን ለመከታተል ፍርድ ቤት መቅረብ የጀመርን ሲሆን “ በክስ ሂደቱ አራቱን ወራት በእስር ቤት እንድናሳልፍ ተገደናል” ሲል ተናግሯል።

እንደ ምስጋና ገለፃ አምስቱም ጋዜጠኞች ተመሳሳይ ክስ የቀረበባቸው ሲሆን ጉዳያቸው ግን በተለያዩ የክስ መዝገቦች ነው የተከፈተው። ምስገና ተሸመ ተማለው እና  ኃይለሚካኤል ገሠሠ በአንድ መዝገብ የተከሰሱ ሲሆን ሀበን ሀለፎም እና ዳዊት መኮንን ደግሞ በሌላ መዝገብ የተከሰሱት ናቸው።

ፍርድ ቤቱ በአንድ መዝገብ ክስ ከተመሰረተባቸው ሶስት ጋዜጠኞች ውስጥ ምስገና እና ተሸመን እንዲለቀቁ ያደረገ ሲሆን ሀይለሚካኤል ገሰሰ ግን በእስር ላይ የገኛል፡፡ ከሀበን ጋር በአንድ መዝገብ ላይ የነበረው ዳዊት መኮንን የተፈታ ሲሆን ግን አለመፈታቱ ተገልጧል፡፡ ፍርድ ቤቱ የመከላከያ ምስክራቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ለጥር 10 አዟል፡፡

የሀይለሚካኤል ገሠሠ ተከላካይ ጠበቃ አብርሃ ካኅሰይ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ፍርድ ቤቱ ያለክስ ለረጅም ጊዜ ጋዜጠኞችን ማሰርን የሚከለክሉትን የኢትዮጵያም ሆነ የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ህግጋትን አላከበረም ብለዋል፡፡

“ከህጉ በተቃራኒ ደንበኛዬ ክሱ ከመጀመሩ በፊት አራት ወራትን ያሳለፈ ሲሆን ክሱ ከተነበበ በኋላ ደግሞ ተጨማሪ አራት ወራትን እንዲያሳልፍ መደረጉ ትክክል አይደለም” ያሉት አቶ አብርሃ፣ የችሎት ቀጠሮዎችም የዘገየ ነው ይህም የፍርድ ቤት አሰራርን ያልተከተለ ነው ብለዋል፡፡  

በየትኛውም የተጠርጣሪ ክስ መመስረት የተለመደ ነው ግን ያለ ምንም ወንጀል ለስምንት ወራት ታስረን መቆየታችን ኢፍትሃዊ ተግባር ነው ያለው ምስጋና ምንም እንኳ በፖሊስ ጣቢያው በመፀዳጃ ቤት ውስጥ የንፅህና ችግር እና ሻወር ችግር ቢኖርም የደረሰብን ጥቃት ግን የለም ብሏል፡፡

በትግራይ ቴሌቭዥን በነበራቸው ቆይታ ሀበን ነባር ጋዜጠኞች ሆኖ ያገለገለ ሲሆን ሀይለሚካኤል ደግሞ  ዜና አንባቢ እና የኦንላይን አርታዒ በመሆን አገልገሏል፡፡ ምስጋና  የትምህርት ዝግጀት ዳይክተር እንዲሁም ተሸመ፣ የሀገር ውስጥ እና የአለምአቀፍ ቋንቋ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ደዊት የመስክ ዘጋቢ ሆኖ ሲያገለግል ነበር፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.