አዲስ አበባ ፣ ኅዳር 29/2014-አክቲቪስት እና ኡቡንቱ’ የተሰኘ ዩቲዩብ ሚዲያ መስራች እያስፔድ ተስፋዬ ህዳር 28 2014 ዓ.ም ከቤተሰቦቹ ቤት መታሰሩን ወላጅ እናቱ ለቢቢሲ አማረኛ ተናገሩ ፡፡ እረፋድ ላይ ወደ መኖሪያ ቤታቸው የመጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ እንደሆኑ የተናገሩት መኖሪያ ቤታችንን ከፍተሹ በውሀላ እያስፔድን ይዘውት ሄደዋል ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ተሻለች ቡልቻ የእያስፔድ ወላጅ እናት እንደተናገሩት ልጃቸትው የት እንዳታሰረ ከቤት የወሰዱት ፖሊሶች አልነገሩኝም ብለዋል አክለውም የት እንደሚወስዱት ስጠይቃቸው ፖሊሶቹ ይቆጡ ነበር ብለዋል ። የእኔ እና የእነሱ መጋጨት ልጄን ያስጨንቀብኛል ብዬ ዝም አልኩ ብለዋል፡፡
ተጨማሪ የእያስፔድ የቤተሰብ አባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ለቢቢሲ አማረኛ እንደተናገሩት ከአዲስ አበባ ፖሊስ የመጡ የፀጥታ ኃይሎች በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ፍተሻ ማካሄዳቸውን እና በመጨረሻም እያስፔድ ለጥያቄ እንደሚፈለግ በመጥቀስ ይዘውት እንደሄዱ ተናግረዋል። የፖሊስ አባላቱ ፍተሻ ከማድረጋቸው በፊት ለረጅም ሰዓታት ትዕዛዝ እየጠበቁ እንደሆነ በመናገር ሲጠባበቁ መቆየታቸውን ይናገራሉ፡፡
በተጨማሪም ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት የእያስፔድ የቤተሰብ አባል እያስፔድ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ግምታቸውን ሰጥተዋል።
አገሪቷ ላይ ተፈጻሚ እየሆነ በሚገኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያትም የፀጥታ አባላቱ መኖሪያ ቤታቸውን ለምን እንደሚፈትሹ እና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደያዙ መጠየቅ አለመቻላቸውን የእያስፔድ እናት ወ/ሮ ተሻለች ቡልቻ ጨምረውም የፀጥታ አካላቱ ከብዙ ሰዓት ፍተሻ በኋላ እያስፔድ የሚጠቀምባቸውን ላፕቶፕ ኮምፒዩተር እና ሞባይል ስልክ መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡ለደህንነቱ ሲባል ስሙ እንዳይተቀስ የለገው የእያስፔድ ጓደኛ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው እያስፔድ አራዳ ክለከተማ የሚገኘው 3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰረ ተናግሯል፡፡ አ.ስ