በማህሌት ፋሲል
አዲስ አበባ፡ነሐሴ 11 2013-የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና የህገመንግስት ጉዳዩች ችሎት በነ እስክንድር ነጋ ላይ የሚሰማው የአቃቤ ህግ ምስክሮች በግልፅ ችሎት እንዲሰሙ በድጋሚ ትእዛዝ ሰጠ፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና የህገመንግስት ጉዳዩች ችሎት ለምስክሮቼ ደህንነት ሲባል ምስክሮቼን በዝግ ችሎት እና ከመጋረጃ ጀረባ ላሰማ ሲል ለችሎት ያቀረበውን አቤቱታ የተከሳሾችን መብት ይጋፈል ሲል ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገበት፡፡
ጠቅለይ አቃቤ ህግ ምስክር አሰማሙ ላይ በተሰጠውን ውሳኔ ቅር በመሰኘት ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መጋቢት ወር ላይ ይግባኝ ቢልም ችሎቱ ጉዳዩን መልሶ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲመለከተው ትእዛዝ በሰጠው መሰረት የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በድጋሚ የአቃቤ ህግን አቤቱታን በድጋሚ ተመልክቶ ምስክሮችን በዝግ ችሎት ወይም ከመጋረጃ ጀርባ ማሰማት የተከሳሾችን መብት የሚጋፋ ሆኖ ስላገኘሁት የአቃቤ ህግን አቤቱታ ውድቅ አድርጌዋለሁ ሲል ውሳኔ ሰቷል ፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና የህገመንግስት ጉዳዩች ችሎት በነ እስክንድር ነጋ ላይ የሚሰማው የአቃቤ ህግ ምስክሮች በግልፅ ችሎት ለመስማት ለሀምሌ 8 ፤9 ፤ 14፤ 15፤16 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል፡፡AS