ግንቦት 25 ቀን፣ 2014 ዓም፤ አዲስ አበባ፡-በየሳምንቱ በአማርኛ ቋንቋ የምትታተመው “ፍትህ” መጽሄት ባለቤት እና ማኔጅንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ በማረሚያ ቤት ቤተሰቦቹን በሚያናግርበት ወቅት በፖሊሶች እንደተደበደበ ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገረ።
ዛሬ ረፋድ ላይ ወንድማቸውን ለመጠየቅ እርሱ እና ታላቅ ወንድሙ እንዲሁም ሁለት ጓደኞቹ 3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ በተለምዶ 3ኛ ተገኝተው እንደነበር የተናገረው ታሪኩ ከተመስገን ጋር መደማማማጥ ስላልቻሉ ተጠግቶ እንዲያወራቸው ጠባቂ ፖሊሶችን በጠየቀበት ወቅት በሁለት ፖሊሶች ተደብድቧልበ ብሏል።
በርካታ ጠያቂዎች ባሉበት እንደመቱት የገለፀው ታሪኩ በቢሮ በኩል ወንድሙን ሲያገኘው ግራ አይኑ አብጦና ልብሱ ተቀዶ ነበር ብሏል ። ሀላፊዎችን ለማናግር ብንሞክርም ከቅጥር ግቢው አባረውናል ሲል ጠበቃው ጉዳዩን እንደሚከታተል ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ”ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት፣ህዝቡ በመከላከያ ሰራዊት ላይ እንዲሁም በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ እና እንዲያምፅ በመንቀሰቀስ” ጠርጥሬዋለው ሲል ፖሊስ ሀሙስ ግንቦት 18 ረፋድ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታውቃል። ክሱንም በፍርድ ቤት እየተከታተለ ይገኛል። አስ