ትንታኔ፡ አዲስ አበባ ከተማ እየተስተዋለ ያለው የዋጋ ንረት የመንግስት ሰራተኛውን ለከፋ የኑሮ ውድነት ዳርጎታል፤ አኮኖሚስቶች መንግስት ገንዘብ ማተም እንዲያቆም አሳሰቡ

የአትክልት ገበያ በአዲስ አበባ

በብሩክ አለሙ @Birukalemu21

አዲስ አበባ፣ ጷጉሜ 4/2014 ዓ.ም፡– በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ እየተስተዋለ ያለው የዋጋ ንረት ቋሚ ገቢ ያላቸውን የመንግስት ሰራተኛውን ለከፋ የኑሮ ውድነት ዳርጎታል፡፡ በወረሃ ነሐሴ 2014 ዓ.ም ”ስታትስታ” ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረት ከአሰራ አምስት ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ካስመዘገቡ የአፍሪካ ከተማዎች ውስጥ አዲስ አበባ 50.49 የኑሮ ውድነት ጠቋሚ ነጥብ በማስመዝገብ የሁለተኝነት ደረጃን ይዛለች፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የተመዘገበው ይህ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በከተማዋ ውስጥ እንደ መኖሪያ ቤት፣ ምግብ፣ ግብር እና የጤና አጠባበቅ የመሳሰሉ መሰረታዊ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያስፈልገው በአማካኝ የገንዘብ መጠን ተሰለልቶ ከፍተኛ በመሆኑ ነው። ይህ የኑሮ ውድነት ጠቋሚ ነጥብ (The cost of living index) በአንድ ከተማ ውስጥ መኖር ምን ያህል ውድ እንደሆነ ለማነፃፀር የሚረዳ ሲሆን በዚህም መሰረት አዲስ አበባ ያስመዘገበችው የኑሮ ውድነት ጠቋሚ ነጥብ(50.49) በከተማዋ ውስት ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መኖሩን ያረጋግጣል፡፡

የአንድ ከተማ የኑሮ ውድነቱት ከነዋሪዎቹ ደሞዝ ጋር የተያያዘ ነው። በአንድ ከተማ ውስጥ ወጪዎች ወይም የፍጆታ እቃዎች ክፍያ ከፍ ያለ ከሆነ የደመወዝ ደረጃዎች ከፍ ያለ መሆን አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በከተማው ውስጥ የኑሮ ውድነቱ ያየለ ይሆናል፡፡

በአዲስ አበባ የመንግስት ሰራተኖች የደመወዝ ስኬል መሰረት የደረጀ አንድ 1100 ሲሆን የመጨረሻው ደረጋ ጣሪያ ደግሞ 26959 ብር ነው፡፡ አዲስ ስታንዳርድ ከአፍሪካ በኑሮ ውድነት የቀዳሚነት ስፍራውን የያዘችው አዲስ አበባ በውስጧ የሚኖሩ የመንግስት ሰረተኞችን አነጋግራለች፡፡

አቶ ሽመልስ መገርሳ ላለፉት 7 አመታት በአዲስ አበባ የሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በከተማዋ እየተስተዋለ ያለው የዋጋ ግሽበት ክፉኛ እያሳሳባቸው ብቻም ሳይሆን የመኖር ህልውናቸውን እየተፈታተነ እነንደሚገኝ ከአዲስ ስታንዳር ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡ እንደ እሳቸው ገለፃ በሚያገኙት ደመመዝ የቤት ክራይ ከፍለው፣ አስቤዛ ገዝተው፣ የሚተርፍ ዘንዘባ ባለመኖሩ ሁለቱን ልጆቻቸውን አስተምሮ ለቁምነገር ማድረስ አዳጋች ሆኖባቸዋል፡፡

አቶ ሽመልስ ባለቤቴ ወሩን ሙሉ ፅዳት ሰርታ የምታገኘው 2000 ብር ከእኔ ደመመዝ ጋር ተደምሮ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ማሟላት አልቻልም ሲሉ ያሉበትን የኑሮ ሁኔታ ያስረዳሉ፡፡ አክለውም በዚ ሁኔታ መቀጥል ስለሚከብደ የመምህርነት ስራየን በማቆም አነስተኛም ብትሆን የግል ስራ ለመስራት ወስኛለው ብለዋል፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ተቀጥረው ኑሮአቸውን በመግፋት ላይ የሚገኙት ወይዘሮ ዝናሽ (ስማቸው እንዲገለፀ ስላልፈለጉ የተቀየረ) እንደገለፁት የኑሮ ውድነቱ በሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ላይ የተከሰተ ቢሆንም ይበልጥ ግን የመንግስት ሰራተኞችን ለከፋ ችግር ዳርጓል ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል፡፡ ወ/ሮ እልፍነሽ የዋጋ ግሽበቱ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው መግስት ወይ ለሰራተኛው ደመመዝ መጨመር ወይም ደግሞ የሸቀጦችን ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግ አለበት ሲል በምሬት ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው ስሙ እና መስሪያ ቤቱ እንዳይጠቀስ የፈለገ የመንግስት ሰራተኛ እንደገለፀው ወቅቱ የበአል ሰሞን ስለሆነ በሸቀጦች ላይ ጭማሬ እየተደረገ ነው፡፡ “በስምንት ሺ ብር መኖር ከብዶኛል ወሩ ሳልቅ ብር ይቸግርኛል፡፡ የመንግስት ሰራተኛን ችግር መንግስት አልተረዳውም፡፡ የምናደርገው ነገር ግራ ገብቶናል” ሲል ስላለው ችግር ገልጧል፡፡

የሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት

ኢትዮጵያስታቲስቲክስ አገልግሎት ይፋ ባደረገው ሪፖረቱ የዋጋ ግሽበት በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ብቻ ሳይሆን የአደጉ ሀገራት ጭምር ፈተና እየሆነ መምጣቱን ጠቅሶ በሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም ወር የምግብ የኢንዴክሱ ክፍሎች መጠነኛ መረጋጋት ያሳዩ ሲሆን ምግብ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች ላይ ጭማሪ ታይቷል ብሏል፡፡ በሪፖርቱ መሰረተት ባለፈው ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 34.0 ደርሶ የነበረ ሲሆን በሐምሌ ወር 2014 ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 33.5 ከመቶ ሆኗል። በዚህ ወር የዋጋ ግሽበቱ መጠን ዝቅ ያለበት ምክንያት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት መጠን በአንጻራዊነት ፈጣን ዕድገት አሳይቶ ስለነበር ነው ያለው ስታቲስቲክስ አገልግሎቱ ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች በያዝነው ወር የመጨመር ሁኔታ አሳይቷል ብሏል፡፡

ስታቲስቲክስ አገልግሎቱ ባለፉት 12 ወራት የዋጋ ጭማሪ የታየ ቢሆንም ጭማሪው ከወር ወር በተመሳይ ሁኔታ የጨመረ መምጣቱን ጠቅሶ ጭማሪው ዋጋን ለማረጋጋት የተወሰዱ እርምጆች የከፋ ጉዳት እንዳይርስ ከፍተኛ አሰተዋጽኦ አድርገዋል ሲል ያስረዳል፡፡ ባለፉት 2 ወራት አጠቃላዩና የምግብ ዋጋ ግሽበት መጠን ላይ መጠነኛ ቅናሽ አሳይተዋል፡፡ ሆኖም ምግብ ነክ ያልሆኑት የዋጋ ግሽበት መጠን ባለፉት ጥቂት ወራት መጠነኛ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጧል፡፡

ሐምሌ 2013 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 26.4 ሲሆን ከአንድ አመት ውስጥ ማለትም ሐምሌ 2014 ዓ.ም ወደ 33.5 ክፍ ብሏል፡፡በተመሳሳይ መልኩ ሐምሌ 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጠቅላላ የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክ 228.8 የነበረ ሲሆን ሐምሌ 2014 ዓ.ም. ወደ 300.6 ክፍ ብሏል፡፡

ይህ ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው የወጋ ግሽበቱ በከፍተኛ መጠን አየጨመረ መምጣቱን ነው፡፡

በአዲስ አበባ የጎዳና አትክልት ነጋዴ ደንበኞቹን እየጠበቀ።

የዋጋ ግሽበቱ ምክኒያትና በመንግስት መወሰድ ያለበት ውሳኔዎች (መፍትሄዎች) በኢኮኖሚስቶች

የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ የምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው አሁን ላይ ላለው የዋጋ ንረት ቀዳሚው ምክንያት ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ በቀጥታ ሸማቹ ላይ እንዲያርፍ መደረጉ ነው ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ አክለውም መንግስት የገበያስ ርዓቱን ለውጭ ኩባንያዎች ክፍት እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የአንዳንድ ምርቶች ዋጋ ማለትም በብረት፣ ዘይት፣ ነዳጅና የመሳሰሉት ከውጭ የምናስገባቸው ምርቶች ዋጋቸው እስከ እጥፍ መጨመር በሀገር ቤት ያለው የጸጥታ ሁኔታም በምርት አቅርቦት ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል የፈጠረና በዋጋ ንረቱ ላይ ትልቅ አበርክቶ አሳርፏል ብለዋል፡፡ አክለውም “መንግስት ወጪውን እየሸፈነበት ያለው የገንዘብ ፖሊሲም በራሱ ጫና የሚፈጥር ነው፤ እነዚህን በጊዜ ሂደት እያስተካከልን መሄድ ካልቻልንም የባሰ ሊመጣ ይችላል” ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ምንስትር ዴኤታው የሀገሪቱ የገበያ ስርዓት በጥቂቶች ብቻ ያለ በመሆኑ መንግስትን የፈጠነ ማሻሻያ እንዲያስብ እንዳደረገው ተጠቁሟል፡፡ ለዚህም የገበያ ስርዓቱ ለውድድር ክፍት መሆን አለበት ያሉት ዶክተር ዕዮብ ዘርፉ ለውድድር ክፍት ሲሆን 200 በመቶ ካላተረፈ ያላተረፈ የሚመስለው ነጋዴ ወደ ቀልቡ እንዲሰበሰብ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የቴሌኮም ኢንዱስትሪው ለውድድር እንደተከፈተ ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ በቅርቡ ደግሞ የሀገሪቱ የግብይት ስርዓት ለዓለም አቀፍ የንግድ ኩባንያዎች ክፍት እንደሚደረግ ነው ያስታወቁት።

ከእነዚህ ምክንያቶች ባለፈ ግን በዶላርና ብር መሃል ያለው የምንዛሬ ተመን በየጊዜው እንዲሰፋ መደረጉ ለዋጋ ንረቱ ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳለውም ገልፀዋል፡፡

“የውጭ ምንዛሬ ላይ የጀመርነው ማሻሻያ የጎንዮሽ ጉዳት የለውም የሚል የመንግስት አካል የለም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ነገር ግን ሊያመጣ የሚችለውን ተጽዕኖ ተቋቁሞ የሚገኘውን ጥቅም ማሳካት ያስፈልጋል፤ ማሻሻያው መዘግየቱ በራሱ የፈጠረው ተጽዕኖ አለ፤ ያን በፍጥነት ተግብረን ችግሮችን ለመቅረፍ እንሰራለን” ብለው ነበር። ማሻሻያው በተለይም በወጪ ንግድ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አስገኝቷል ቢባልም ችግሮች በተደራረቡ ጊዜ ግን አንዳንድ ማሻሻያዎችን ማዘግየት እንደ መፍትሄ ይቆጠራልም ነው ያሉት፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፈሰር አጥላው አለሙ የዋጋ ግሽበቱ ምክኒያት መንግስት ገንዘባ እያተመ ማስገባቱ ነው ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል፡፡ መንግስት እኮኖሚው ከሚችለው በላይ አየታተመ ወደ አገር ውስጥ የሚገባውን ገንዘብ ካላቆመ እየተባባሰ በሚመጣው የዋጋ ንረት የመንግስት ሰራተኛው እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ተጎጂ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡ ብሔራዊ ባንክ በኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የገንዘብ መጠን የመቆጣጣር ስልጣን እያለው ገንዘብ እንዳይታተም ከማድረግ ዝምታን መርጧል፤ በዚም የተነሳ መንግስት እዳ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋ ሌላ ችግር ያስከትላል በማለት አስረድተዋል፡፡

በኢኮኖሚ ውስጥ የተትረፈረፈ ገንዘብ ከሌለ በስተቀር ነጋዴው ገዥ ስለማይኖርው ሊጨምር አይችልም ያሉት ኢኮኖሚስቱ በምሳሌ ሲያስረዱም ከአመት በፊት በአንድ ቢሊየን ብር የተገዛ እቃ ዘንድሮ በሁለት ቢሊየን ብር ከተገዛ የታተመ ገንዘብ በመኖሩ ነው ይላሉ፡፡ በዚም የተነሳ የመግዛተት አቅም ያላቸው በተባሉት ወጋ ሲገኙ በቂ የሆነ ገቢ የሌላቸው የምንግስት ሰራተኞች እና ሌሎች አካላት ላይ ኑሮ እንዲወደድባቸው ያደርጋሉ ስለዚህ መንግስት እያተመ የሚያስገባውን ገንዘም ማቆም አለበት ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የዘንድሮው የዋጋ ግሽበት ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚደርስ መሆንን የጠቀሱት ሌላኛው ኢኮኖሚስት አዲሱ አበባው ይህ የሆነበት በሀገሪቱ ውስጥ አየተካሄደ ያለው ጦርነት ምርትን እንዲቀንስ ማድረጉ አንዱ ምክኒያት ነው ሲሉ ገፀውልናል፡፡ መንግስት ያለአግባብ የሚያወጣው ወጪም አስተዋእፆ እንዳለው ነው አክለው የጠቀሱት፡፡ “መንስት በዚህ ወቅት አስፈላጊ ባልሆኑ ነገሮች ላይ ወጪ እያወጣ ነው ይህ ደግሞ ገንዘብ አትሞ እንዲያሰገባ ስለሚያደርግ የዋጋ ግሽበቱ እንዲባባስ ያደረጋል፤ ለምሳሌ መዝናኛ ላይ የሚያውለው ገንዘብ ለጊዜው አቁሞ ህብረተሰቡ ህልውናውን የሚያቆይበት ምግብና የመሳሰሉት ላይ ማዋል አለበት” ብለዋል፡፡

“ትልቁ የመንግስት ችግር ሀገር ውስጥ ሊመረት የሚችሉትን ምርቶችን ከውጭ ማስገባቱ ነው”

አዲሱ አበባው

አክለውም “በዩክሬን እና በራሽያ መካከል ያለው ጦርነት የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ምክኒያት በመሆኑ የምርት ዋጋም ሊጨምር ችሏል፡፡ ይህም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንና የመንግስት ሰረተኛው ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንዳደረሰ ጠቅሰው ዋጋ ጨመረ ማለት ገቢ ቀነሰ ማለት ነው፣ ቋሚ ገቢ ያላቸው እየደሀዩ ሲመጡ ነጋዴዎች ግን የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ እድል ስለሚፈጥርላቸው የገቢ አለመመጣጠን ይፈጠራል፡፡ የዋጋ ግሽበት በጨመረ ቁጥር ታክስ ይቀንሳል መንግስትም በታክስ የሚያገነው ገቢ ያልተረጋጋ እንዲሆን ስለሚደርግ መንግስት ወደ ገንዘብ ህትመት እንዲገባ በማድረግ እንደገና ግሽበቱ እንደባባስና ህዝቡ ለከፋ ኑሮ ውድነት እንዲጋለጥ ያደረጋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

አቶ አዲሱ እንደገለፁት የዋጋ ግሽበቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ የሆነ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ያስፈልገዋል በተለይ የሸቀጣ ሸቀጠችን ወጋ ማረጋጋት ይኖርበታል፣ በሸማቹ እና በሸጩ መካከል ያለውን የግብት ሰንሰለት ማጥበብ አለበት፡፡ ገበሬው በቀጥታ ለሸማቹ እንዲያቀርብ መደረግ የአጭር ጊዜ መፍትሄ ሊሆን እንዲችል ተናግረዋል፡፡

“ትልቁ የመንግስት ችግር ሀገር ውስጥ ሊመረት የሚችሉትን ምርቶችን ከውጭ ማስገባቱ ነው” ያሚሉት ኢኮኖሚስቱ ሸክላ ሳይቀር ከውጭ ማስገባታችን የሀገር ውስጥ አምራችን በማዳከም የምርት መቀነስንና የዋጋ ግሽበትን የሚያስከትል በመሆኑ ምርትና ምርታማነት ላይ በደንብ መሰራት አለበትም ብለዋል፡፡

በጦርነቱ ባስከተለው የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር የተነሳ በመቶ የሞቆጠሩ ፋብሪካዎች ስራ አቁመዋል፣ ብዙ ሺ ሄክታር መሬት ሳይታረሱ ቀርተዋል፡፡ ስለዚህ የሰላም እጦት የምርት መቀነስን በማስከተል ለኑሮ ውድነቱ ትልቅ አስተዋዕፆ እየተጫውተ በመሆኑ አነዚህ ነጥቦች ላይ መንግስት በትኩረት መስራት አለበት ሲሉም አሳስበዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.