አዲስ አበባ ጥር 23/2014 ከወራት በፊት በምእራብ ጉጂ ዞን በቡሌ ሆራ ፖሊስ ጣቢያ በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ታስረው የሚገኙ ከመቶ በላይ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በታሰርንበት ተረስተናል ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ:: በተላያየ ግዜ ከተለያየ ቦተ እንደታሰሩ የተናገሩት እስረኞች ፍርድ ቤትም ቀርበን ሆነ በመርማሪዎች ጥያቄ ቀርቦልን አያውቅም :: ከሁሉም በላይ ምግብ የሚያቀርብልን የመንግስት አካል የለም ብለዋል :: ቤተሰብ በአካባቢው የሌላቸው በርከት ያሉ ታሳሪዎች አሉ ያሉት ታራሚዎች በከፍተኛ ችግር ላይ ነን መንግስት መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ተማጽነዋል:: አስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከተነሳ በኋላ ሌላ ጣቢያዎች ታስረው የነበሩ ቢፈቱም እኛ ግን እስካሁን በእስር ላይ ነን ሲሉ ተናግረዋል::
እስረኞቹ በምን ምክንያት እንደታሰሩና እስካሁን ከእስር ለምን እንዳልተፈቱ ለአዲስ ስታንዳርድ መልስ የሰጡት የምእራብ ጉጂ ዞን አስተዳደር አቶ ጀንበሩ አበበ “በአሁኑ ሰአት በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ታስሮ የሚገኝ ምንም እስረኛ የለም በአዋጁ የተነሳ ተይዘው የነበሩ 96 እስረኞችን አጣርተን ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ከእስር ፈተናል ብለዋል ። አሁን በእስር ላይ ያሉ መንግሥት ሸኔ ብሎ በሚጠራው እና በሽብርተኝነት በፈረጀው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት ያለቸው ግለሰቦች ናቸው ብለው አስረድተዋል ። “የነሱ እስር ከአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም” ያሉት ጀንበሩ “በዞናችን በተለያየ ግዜ በዞናችን ሽብር ቡድኑ ጉዳዊት እያደረሰ ነው። የቡድኑን አባለትና ሲረዱት የነበሩ ሰዎች አሁንም ታስረው ምርመራ እየተደረገነው ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል ::አስ