ቃለ ምልልስ፡- “ዋነኛ ትኩረታችን በጦርነቱ የተጎዱ ንፁሃንን ማዳን እንጂ በአንድ ወገን በኩል ጫና መፍጠር አልነበረም”- በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል – በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ አምባሳደር (ነዋሪ ያልሆኑ) እና የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ ተወካይ (ምስል = እንግሊዝ ኤምባሲ ዌብሳይት)

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ  የእንግሊዝ አምባሳደር ሲሆኑ ከዚህም በተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ ተወካይ ናቸው። በተለይ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር  ባደረጉት ቃለምልልስ በተፈረመው የሰላም አተገባበርና ዘላቂነት በትግበራ ሂደት የሚያጋጥሙ ማነቆዎች፣ የኤርትራ ጦር እና የአማራ ታጣቂ  ሃይሎች ከስምምነቱ በህዋላም ከትግራይ አለመውጣታቸው፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ግጭቶቹንና በአገሪቱ የኢኮኖሚ ለውጥና የሁለትዮሽ ትብብር ዙሪያ ሰፋ ያለ ሰጥተዋል።  ቃለምልልሱ በሚከተለው መልክ ቀርቧል።

አዲስ ስታንዳርድ፡ በመጀመሪያ የእንግሊዝ እና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት አሁን ያለበትን ሁኔታ ሊያብራሩልን ይችላሉ?

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል፡- እንግሊዝና ኢትዮጵያ ከ100 ዓመታት በላይ የቆየ የረጅም ጊዜ ወዳጅነት አለን። እንግሊዝ አዲስ አበባ ላይ ኤምባሲ ከከፈቱት የመጀመሪያዎቹ ሀገራት አንዷ ነች። ካለፉት ጥቂት አሥርት ዓመታት ወዲህ በዓለም ላይ ትልቁን የልማት ፕሮግራማችን እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ አድርገናል። ከዚህም በተጨማሪ ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እገዛ በማድረግ፣ ለምሳሌ ያህል  ከ2007 ጀምሮ እንግሊዝ 1.2 ሚሊዮን ሕፃናትን ትምህርት እንዲማሩ ድጋፍ እያደረገች ነው።  በእርግጥ ይህንን ቁጥር ማሳደግ አለብን። በሌላ በኩል ደግሞ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የንፁህ ውሃ አቅርቦትና የንፅህና መጠበቂያ ተቋማትን አበርክተናል። እንግሊዝም በተሳተፈችበት ሳፋሪኮምም  በኢትዮጵያ ቴሌኮም እንዲሰራ  ፍቃድ የመስጠት ስራዎችን አከናውነናል። ከዚያ በላይ ግን የህዝብ ለህዝብ እና የመንግስት ለመንግስ አስገራሚ ግንኙነቶች አለን።

አዲስ ስታንዳርድ፡ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ክልል መካከል ለሁለት አመታት የዘለቀ  ደም አፋሳሽ ግጭት ነበር። ግጭቱ በሰላማዊ ድርድር እንዲፈታ በማገዝ ተገድ  የእንግሊዝ ሚና ምን ነበር?

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል በመጀመሪያ ደረጃ ግጭቱን ለማስቆም በፕሪቶሪያ ጥቅምተ 2015 ዓ የመንግስት እና የህወሓት ባለስልጣናት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን እንቀበላለን። ግጭቱ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ሁሌም ያሳስበን ነበር።ከዚያም የአፍሪካ ህብረት ድርድሩን መምራቱን እና ሌሎችም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ደግፈናል። ግጭቱ ከተጀመረበት ከጥቅምት 2013 ዓም ጀምሮ ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች  ግጭቱን  እንዲቆም፣ ሰላማዊ ዜጎች እንዳይጎዱ እና አቅመ ደካሞች ላለመገዳታቸውነ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ከመንግስት እና ከህወሓት አካላት ጋር ተከታታይ ግንኙነት ስናደርግ ቆይተናል። የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይኖሩ እና ለፖለቲካዊ ችግሮች በወታደራዊ መንገድ መፍትሄ እንደማያገኙ አጽንኦት ሰጥተን  ከፌዴራል ለመንግስት እና በመቀሌ ለሚኖሩ ለትግራይ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ለማግባባት ሙከራ ስናደርግ ነበር። የክትትል የማረጋገጥ እና ተገዢነትን ቡድም ምስረታ ላይ ለመገኘትና ባለፈው ሳምንት ወደ መቀሌ ለመህድ እድል አጋጥሞኝ ስለነበር እዚያ ያሉ ሃላፊዎችን ፊት ለፊት ለማነጋገር ችያለሁ፡፡ ባለፈው አመትም  በግጭቱ ወቅት ሄጄ በቀጥታ ከህወሓት ባለስልጣናት  ጋር የመነጋገር እድል አግኝቸ ነበር። የግጭቱ አካል የሆነው የፖለቲካ ጉዳይ በግጭቱ ምክንያት ተባብሶ እንደቀጠለ እና በመጨረሻ ወታደራዊ ድል ለችግሩ መፍትሄ እንደማይሰጥ በመግለጽ ሰላምን ለማበረታታት ከሁለቱም ወገኖች ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት አድርገናል። ጦርነቱ የነበረው ችግርም አልፈታም እንዲያውም በግጭቱ ምክንያት አዳዲስ ችግሮች እንዲፈጠሩ አድርጓል።  ሆኖም ግን በቅዲሚያ  መስተካከል የነበረበት  ትልቅ ስራየሰላም ስምምነቱ ነበር አሁን ስምምነቱ ተከናውኗል።

አዲስ ስታንዳርድ፡ የፌዴራል መንግስት አሜሪካ እና እንግሊዝ ጨምሮ የአውሮፓ ሀገራት በሁለቱም ወገኖች ቅሬታ ይኣርብባቸው ነበር፡፡ የፌዴራል ምንግስት ጫና ተደረገብኝ ሲል የትግራይ ባለስልጣናት ደግሞሁሉም ከበባ እና ግፍ እየተፈጸመ  በነበረበት ወቅት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጆሮ ዳባ ልበስ  ብሏል ሲሉ ቅሬታቸውን እየገለጹ ነበት። ለዚህ ቅሬታ ምን ምላሽ አለዎት?

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል የጠቀስካቸው ሌሎች ሀገራት በሚመለከት መናገር አልችልም ነገር ግን ለእንግሊዝን በሚመለከት ቀደም ሲል  እንደገለፅኩት፣ በግጭቱ ላይ የነበሩትን  ሁሉቱን ወገኖች ጦርነቱን እንዲያቆሙ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ከጥቃት እንዲከላከሉ እና የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲስተካከሉ  እናበረታታ ነበር።ግጭቱን በማቆም ሰላማዊ መፍትሄ እንዲመጣ ጥረት ስናደርግ ነበርን፨

____________________________________________________________________

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፈጠረ የተባለው ማንኛውም ዓይነት ጫና ግጭቱን ለማስቆም፣ ጦርነቱን ለማስቆም፣ ሲቪሎችን እና አቅመ ደካሞችን ለመጠበቅ የተደረገ ነው

ከመጀመሪያ አንስቶ እንደተናገርነው ለፖለቲካዊ ችግር ወታደራዊ መፍትሔ ሊመጣለት አይችልም። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሳደረ የሚባለው ማንኛውም ዓይነት ጫና ግጭቱን ለማስቆም፣ ጦርነቱን ለማስቆም፣ ሰላማዊ ዜጎችን እና አቅመ ደካሞችን ለመጠበቅ ነበር። በአንድ በኩል ጫና ተፈተርብን ከሚሉ በሌላ በኩል ደግሞ   ጆሮ ዳባ ተባልን ብለው ከሚያምኑ ሰዎች ጋር አልስማማም። ሚኒስትሮቻችን በፓርላማችን የተረጋገጠውን ግፍ ሁሉ ተችተዋል።   ስለዚህ እኛ እንሆን ጥረት ሲናደርግ የመበረው ሁለቱ መገኖች ግጭቱን እንዲያቆሙ ከመምከር በዘለለ አንዱ ላይ ጫና ማሳደር ሌላውን መጉዳት የታሰበና የተደረገ ነገር አይደለም። ሁለቱንም ወገኖች በግልጽ እናውቃቸው ስለነበርን የእኛ አካሄድ ከሌሎች አገሮች አካሄድ የተለየ ነበር። ዋናው ያሳስበን የነበረው ጉዳይ የአገሪቱ እጣ ፈንራ ነበር። በሕዝብ እና በዓለም አቀፍ ሕግ ላይ  ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ ነበር። ስለዚህ  አንዱን ወገን ለመጥቀም  ሌላው ለመጉዳት የመሞከር ጉዳይ አልነበረም።

አዲስ ስታንዳርድ፦  የተፈረመው የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እየሆነ ይመስላል ምክንያቱም በዋናነት ባለፉት ጥቂት ቀናት አንዳንድ አዎንታዊ ክንውኖችን አይተናል ነገር ግን አሁንም ያልተስተካከሉ ጉዳዮች አሉ፡የሰብዓዊ ዕርዳታ እና የመድኃኒት እጥረት; የኤርትራ ጦር እና ሌሎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ያልሆኑ ኃይሎች ከትግራይ ያለመውጣትና የሰብአዊ መብት ጥሰት የመሳሰሉት ችግሮች መቆጫ አላገኙም። እነዚህን ሁሉ ማነቆዎች በቀጣይ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት እንግሊዝ ምን ሚና ይኖራታል?

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ የተደረገው ስምምነት የመጨረሻው አይደለም። ተጨማሪ የፖለቲካ ድርድሮች  ይኖራሉ። እስካሁን የተደረጉት አብዛኛዎቹ ድርድሮች ግጭቱን ለማስቆም ታጣቂው ሃይል ምን መደረግ እንዳለበት፣ ከባድ የጦር መሳሪያ በሚመለከት እና የመሳሰሉትን የሚመክር ነበር፡፡ ተጨማሪ የፖለቲካ ድርድር ስለሚደረግ ፖለቲካ ሁኔታው  በምን መሰረት መሆን አለበት የሚለው ነው። በአጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ ከተደረሰው  የሰላም ስምምነት  ትግበራ አናፃት የምናደርገው ድጋፍ ምን መሆን  እንዳለበት፣ የስምምነቱ ድንጋጌዎች ምን እንደሆኑ እና ክትትል፣ማጣራት እና ተገዢነትን ለማደራጀት የሚያስችል የክትትል ዘዴ እንዳለ በጥንቃቄ እንመለከታለን። ሁለቱም ወገኖች  በአጠቃላይ የተፈራረሙትን በማክበር ጥሩ እየሰሩ ናቸው እናም በዚህ ረገድ እነሱን መደገፍ አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ።

____________________________________________________________________

ከሰብአዊ መብት ጥሰት ወዘተ አንፃር፣ ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል ብለን እናምናለን፣ ለተፈጸመው ግፍ ከለላ ሊኖር አይገባም፣ በተመሳሳይም የውጭ ኃይሎች በተለይም የኤርትራ ኃይሎች መኖራቸው ሰላሙን ተግባራዊ ለማድረግ ቀላል ያደርገዋል ብለን አናምንም።

___________________________________________________________________

ዩናይትድ ኪንግደም 54 የጭነት መኪናዎችን ለአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በማቅረብ እርዳታ እና መድሀኒቶችን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ  እየተጠቀመባቸው ነው። ወደ ፊት ለመራመድ ፓርቲዎች የተስማሙበትን ተጨባጭ ፕሮፖዛል ለመገምገም እና የት መደገፍ እንደምንችል ለማየት እንሞክራለን። ከሰብአዊ መብት ጥሰት ወዘተ አንፃር ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል ብለን እናምናለን፤ ለተፈጸመው ግፍም ተጠያቂነት ሊኖር ይገባም፤ በተመሳሳይ መልኩ የውጭ ኃይሎች በተለይም የኤርትራ ኃይሎች መኖራቸው የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ቀላል ያደርገዋል ብለን አናምንም። የኤርትራን ሰራዊት ከትግራይ እንዲወጣ ለማድረግ በተቻለን መጠን እናበረታታለን እዚህ ያለው መንግሥት የኤርትራ ኃይሎች እንዲወጡ ለማሳሰብ። የውጭ ኃይሎች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ይህ በኢትዮጵያውያን ሊፈታ የሚገባው የእውነት የኢትዮጵያ ጉዳይ ሆኖ መገኘቱ ጠቃሚ ይመስለኛል።

አዲስ ስታንዳርድ፡- የአፍሪካ ህብረት ክትትል፣ ማረጋገጫ እና ደንብ ተልእኮውን በመቐለ  ከተማ ሲጀመር ታድመው ነበር። ለመሆኑ እዚያ ምን ታዝበዋል? ለመሆኑ  የተፈረመው የሰላም ስምምነት ዘላቂነት ኖሮት የህዝቡ ስቃይ ያበቃ ይሆናል ብለው ያምናሉ?

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል፡- ሰላሙ የግድ እውን መሆን ያለበት ይመስለኛል። እነሱ፣ የትግራይ ሃይሎች እና የፌዴራል ሃይሎች  ጦርነት አቁመዋል። የውጭ ኃይሎች በአካባቢው መኖራቸው ለክልሉ መረጋጋት ይረዳል ብዬ አላምንም። የሰላም ስምምነቱ ሲፈረም ሁኔታዎች በሙሉ ለአደጋ የተጋለጡ ነበሩ። ዋናው ነገር ጦርነቱ  እንዲቆም ማድረግ ለሁሉም መልካም ነበር የህዝቦችን ህይወት ለማሻሻልም ያግዛል። ያንን አስተሳሰብ ለማስረፅ ሁላችንም የበኩላችንን ሚና ሲንወጣና እና መርዳት ያለብንን ለማገዝ ጥረናል። ከመንግስት እና ከትግራይ ባለስልጣናት ጋር በመነጋገር ሁለቱም ለሰላም ስምምነቱ ቁርጠኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ችለናል። ሰላሙን የሚሹበት አንድ አይነት ምክንያት ላይኖራቸው ይችላል ግን ሰላም ይፈልጋሉ ብዬ አምናለሁ። ወደ ፊት መሄድ ይፈልጋሉ። ሁለቱም ሌሎች ጉዳዮች እንዳሉባቸው  እና ቀደም ሲል እንደተናገርኩት ለፖለቲካዊ ችግሮች ወታደራዊ መፍትሄ  ሊሆን ስለማይችል  ወታደራዊ ሃይል ችግሩን  አይፈታውም ። ሊተኮርባቸው የሚገ ትልልቅ ጉዳዮች አሉ እና በዚች ሀገር  ትልቅ ችግር አለ።በዚህ ላይ ማተኮር ጠቃሚ ይመስለኛል። ኢትዮጵያ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የቀጠናው ሀገራትም ጠቃሚ ሀገር ነች። ስለዚህ የኢትዮጵያ መረጋጋት ለሁሉም ወገን ይጠቅማል። በመሆኑም  በኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋት እና ደህንነት ላይ ብዙ መስራት በቻልን መጠን ልማቷ የተሻለ ይሆናል።

አዲስ ስታንዳርድ፡- እንደሚታወቀው በትግራይ የነበረው ሁሉም ነገር ወድሟል። ዩኒቨርሲቲዎቹ፣ ትምህርት ቤቶቹ፣ የጤና ተቋማቱ፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ፋብሪካዎች፣ መሠረተ ልማቶችና ሌሎች የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት ወድመዋል። በአማራ እና አፋር አካባቢዎችም ጉዳት ደርሷል። በትግራይ መልሶ ግንባታ ላይ የመሳተፍ እቅድ አላችሁ?

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል፡- ደህና፣ የመልሶ ግንባታ ዕቅዶች ምን እንደሆኑ ማየት እንፈልጋለን። በአሁኑ ወቅት ያለብን ችግሩ ትግራይን መጎብኘት ለማናችንም የማይቻልበት ሁኔታ መሆኑ ነው። ለብዙ ወራት መሄድ እና ምን ጉዳት እንዳለ ለመረዳት ስላልተቻለ ምን ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ለማወቅ አልቻልንም። እኔ እንደማስበው ትግራይን መልሶ ለማቋቋም ምን አይነት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሁን ላይ ማንም ሰው በትክክል መናገር አይቻልም። ለትግራይ መልሶ ማቋቋምም ሆነ መልሶ ግንባታ ባለሙያዎች ሄደው የሚፈለገውን ለማየት እንዲችሉ ሰፊ ተደራሽነት እንዲኖር እንጠብቃለን። በትግራይ፣ አማራ እና አፋር በግጭት ለተጎዱ ህጻናት በዩኒሴፍ በኩል የድንገተኛ ጊዜ ትምህርት እና የሳይክል ማህበራዊ ድጋፍ ሰጥተናል። በጤና እና በትምህርት ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ድጋፍ እያደረግን ነው። ይህም በአሁኑ ወቅት ለትግራይ ምንም አይነት ቀጥተኛ ጥቅም የለውም። በአለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ተቋማት እና ድርጅቶች ምን አይነት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የሚፈለገውን ነገር በትክክል መገምገም ይኖርብናል።

አዲስ ስታንዳርድ፡በሰሜን ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ቢደረግም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል ግጭቶችመኖራቸው በኢትዮጵያ ሙሉ ሰላምና መረጋጋት ይመጣል ብለው ያምናሉ?

____________________________________________________________________

እነዚህን  (ግጭቶቹን) ለመፍታት የፖለቲካ ብልህነት የፖለቲካ ፍላጎት፣ ራዕይ እና ክህሎት ያላቸው ሰዎች ያስፈልገዋል። የሀገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ በሰላም ላይ የተመሰረተ ነው። ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ስታስመዘግብ የነበረው አስደናቂ የእድገት ጎዳና ዳግም መመለስ የምትችለው  ብቸኛው መንገድ ይህ ነው። በአለም ላይ ከአስር አመታት በላይ ፈጣኑ ኢኮኖሚ በማደግ ላይ ያለ ነበር እና ወደዚያ ለመመለስ እነዚህ ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል።

___________________________________________________________________

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል፡- በእርግጠኝነት ተስፋ አደርጋለሁ። እውነት ለመናገር በሀገሪቱ ውስጥ ሁሌም ግጭቶች አሉ። ከአራት አመት በፊት ኢዚህ አገር ሲመጣ  በሀገሪቱ ውስጥ በነበሩ  የግጭት ቦታዎች ላይ አጭር መግለጫ ተደርጎልኝ ነበር።  ግጭቶቹ ቢያንስ ስድስተ ነበሩ በኦሮሚያ ውስጥም ሆነ በሌሎች ቦታዎችም ግጭቶች አሉ። በሰሜን ያለው ግጭት እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት እነዚህም  ግጭቶች ተባብሰዋል። ስለዚህ እነዚህን የተለያዩ ግጭቶች ለመፍታት መንግሥትም ሆነ ሌሎች፣ ወይም ፖለቲከኞች፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በአንድነት በመሰባሰብ መፍታት እንደሚችሉ ተስፋ አደርጋለሁ። እነዚህን ለማየት (የግጭት አፈታት) የፖለቲካ ቁርጠኝነት ፣ የፖለቲካ ፍላጎት፣ ራዕይ እና ክህሎት ያላቸው ሰዎች ሊኖሩት ይገባል። የሀገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ በሰላም  ላይ የተመሰረተ ነው። ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም በባለቤትነት ለነበረው አስደናቂ የእድገት ጎዳና ደጋፊ የምትሆንበት ብቸኛው መንገድም ይህ ነው። በአለም ላይ ከአስር አመታት በላይ በፈጣኑ ኢኮኖሚ እድገት  ላይ የነበረች አገር ነች  እና ወደዚያ ለመመለስ እነዚህ ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል።
አዲስ ስታንዳርድ፡- የኢትዮጵያ ሰላም ለቀጣናው ሀገራት ጠቃሚ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ ስላለው ሰላምና እና መረጋጋት የእርስዎ ግምገማ እና ምልከታ ምን ይመስላል?
አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል፡- ልክ እንደ ብዙዎቹ የአለም ቦታዎች በሰላም እና ደህንነት እጦት ምክንያት የአፍሪካ ቀንድ አገራትንም ጫና ውስጥ ናቸው። በመደበኛነት የምናየው  ይህ ነው። ኢትዮጵያ በራሷ ድንበር ሰላምና ደህንነትን ማግኘት እንድትችል በቀጠናውም ቀደም እንደነበረችው እንደገና ወሳኝ እንድትሆን ያስፈልጋል። ድንበሮች በአግባቡ ስላልተከለሉ ብዙ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ድንበር አቋርጠው ይሄዳሉ። ባለፈው አመት አልሸባብ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ያየነውንጉዳይ ነው። በሶማሊያ በየትኛውም ቦታ የጸጥታ ችግር አለ።  ዩናይትድ ኪንግደም በሶማሊያ የሚገኘውን የአፍሪካ ህብረት የሰላም ዘብ አሚሶም የገንዘብ ድጋፍ አበርክታለች። በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደህንነትን ለማስፈን አስፈላጊውን ነገር እንረዳለን ምክንያቱም ቀጠናው ብዙ ተግዳሮቶች አሉበት። እኔ እንደማስበ በእያንዳንዱ አገር ውስጥ በተናጥል ከሚታየው ጥረት ይልቅ ክልላዊ ጥረቶች  ሊኖሩ ይገባል ምክንያቱም ብዙዎቹ የሰላምና የጸጥታ አደጋዎች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው ድንበር ተሻጋሪ ቡድኖችን ያካተቱ ናቸው።  አንዳንድ የፖለቲካ መሪዎች እነዚህን ለመፍታት ሲሞክሩ ቆይተዋል። ነገር ግን በአገሮች ብቻ ሳይሆን በአጋሮች፣ በአፍሪካ ዩኒየን፣ ክልላዊ ድርጅት ይህንን ክልላዊ ጉዳይ አንድ ሀገር ብቻ ሳይሆን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የላቀ ትብብር እና ቅንጅት ያስፈልጋል።
አዲስ ስታንዳርድ፡ መልካም አምባሳደር አገሪዎ እንደ አጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ምን ዓይነት ፍላጎት አላት?
አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል፡- ብዙ ፍላጎቶች አሉን በተለይ ደግሞ ከአገሮች ጋር ሽርክና እና ጓደኝነትን እንዴት መፍጠር እንደምንችል ነው። በዚህ አገር እና በዚህ ቀጠና ውስጥ ብዙ ፈተናዎች አሉ። ድርቅ እና የምግብ ዋስትና እጦትን ያስከተለው ለአመታት የሚቋረጠውን  ዝናብ ተመልከት። በዚህ ክልል ውስጥ  ብዙ ለችግር ተጋላጭ ሰዎች አሉ። እንግሊዝ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተወሰኑ አመታት ትልቁን የሁለትዮሽ የልማት መርሃ ግብር አላት። እዚህ ካሉት ዋና ዋና ፍላጎቶች አንዱ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን የህይወት እድሎችን መክፈት ነው። በዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ ደጋግሜ እንዳልኩት የኢትዮጵያ ደህንነት እና መረጋጋት ለሰፊው ለቀጠናው ወሳኝ ነው እና ሰላም ሲኖር እኛንም ይጠቅማል። በእርግጥ በዩናይትድ ኪንግደም ድህነትን ለመቀነስ ለመርዳት ህጋዊ ግዴታና ቁርጠኝነት አለን።  በቅርቡ ከገባንበት የቴሌኮም ስምምነት ያየነው ይህ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የበለጠ የንግድ ስራ ለመስራት እንፈልጋለን። ለዚህ ደግሞ ሰላም ያግዘናል። ችግሮችን በመፍታት ዙሪያ ከተንጠለጠለው ግንኙነታችንወደ አወንታዊ ጉዳዮች ማሸጋገር  እንፈልጋለን።

አዲስ ስታንዳርድ፡ በጣም አመሰግናለሁ አምባሳደር አላስታይር። በመሰረቱም ሆነ  በኦሮሚያ ክልል የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት የፌደራል መንግስት ምን ማድረግ ይኖርበታል? ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልእክት ካለዎት?

አምባሳደር ዶክተር አልስተር መክፊል፡- መልካም ፣ ሚኒስትሮጩን አገኛቸዋለሁ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩም በተደጋጋሚ ጊዜ አገኛቸዋለሁ። ይህንን መልእክት ለእነሱም እሰጣቸዋለሁ። ሆኖም ይህች ሀገር ትልቅ አቅም ያላት አስደናቂ ሀገር ናት። ይህንን አቅም እውን ማድረግ የሚቻልበት ብቸኛ መንገድ የሰላም ሀገር መሆን ስትችል ነው። ከዚህ በፊት ስታስመዘግብ የነበረውን አስደናቂ ልማት እንዲቀጥል እንመክራለን። ስለሆነም ይህችን ትልቅ አቅም ያላትን አስደናቂ ሀገር በአግባቡ ለመጠቀም የሚጠቅሙ ሁሉም ዓይነት ጉዳዮች በወታደራዊ መንገድ መፈታት አይችሉም ብዬ አሁንም ደግሜ መልእክቴን አስተላልፋለሁ። ሰላምን ማእፈን፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሮፎርሞችን ማድረግ እንዲሁም ሁሉም ሰው ወደፊት ድርሻ አለኝ ብሎ በሚሰማው መልኩ እውነተኛ እና ሁሉንም ያሳተፈ ሀገራዊ ውይይት መፍጠልጋል። በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ግጭት መቀነስ በተቻለ  ቁጥር ህዝቡ እርስ በርሱ ይግባባል አንድነቱን ያጠናክራል ምክንያቱም የዚህች ሀገር ብዝሃነት በጣም አስደናቂ በመሆኑ ይህንን መጠቀም በእጅጉ ጠቃሚ ነው።አስ
No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.