ዜና፡ የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች መምህራን ወደ ክልሉ ለመመለስ ባለመቻላቸው በአዲስ አበባ እንዲቆዩ መደረጋቸውን ተናገሩ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 1/2015 ዓ.ም፡- በዘንድሮ 2015 ዓ.ም ትምህርት አመት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመፈተን በተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች ተመድበው የነበሩ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች መምህራን ወደ ክልሉ መመለስ ባለመቻላቸው በአዲስ አበባ እንዲቆዩ መደረጋቸውን መምህራኑ ለአዲስ ስታንዳረድ አስታወቁ። “በአማራ ክልል ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ በመደበኛ የሕግ ማስከበር ስርዓት ለመቆጣጠር