ዜና፡ በአፋር ክልል በተከሰተ የደንጊ ትኩሳት ወረርሽኝ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2015 ዓ.ም፡- በሰሜናዊ ምስራቅ የአፋር ክልል አከባቢ በተከሰተ የደንጊ ትኩሳት ወረርሽኝ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የአለም የጤና ድርጅት ይፋ ባደረገው ሳምንታዊ ሪፖርቱ አስታወቀ። እስከ ግንቦት 13 ቀን 2015 በአጠቃላይ 1638 በደንጊ ትኩሳት ወረርሽኝ በሽታ የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን ያመላከተው ሪፖርቱ በሽታው በስፋት የተሰራጨው በሚሌ