ዜና፡ ለስምንት ወራት በእስር ላይ ከነበሩ አምስት የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች ሶስቱ ተፈቱ፤ የተከሳሽ ጠበቃ በፍርድ ቤት አሰራር ላይ ቅሬታ አቅርበዋል
በምህረት ገ/ክርስቶስ @MercyG_kirstos አዲስ አበባ፣ ጥር 9/2015 ዓ/ም፡- መቐለ የሚገኘው ፍርድ ቤት “የጠላትን ፕሮፓጋንዳ አሰራጭተዋል” ተብለው በአካባቢው ባለስልጣናት ከተከሰሱ አምስት የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች መካከል ሦስቱ ከስምንት ወራት የእስር ቆይታ በኋላ እንዲለቀቁ አድርጓል፡፡ ምስጋና ስዩም ባሳለፍነው ሳምንት ከእስር ከተለቀቁት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ሲሆን ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው ከህዳር 28 እስከ