ዜና፡ ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት የማያስከብር ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ምእመናን የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ አስታወቀ፤ ጠ/ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሰጡት ማብራሪያ ላይ እርምት እንዲሰጡ አሳሰበ
አዲስ አበባ፣ጥር 25/ 2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልዕልና እንዲያስጠብቅ እንዲሁም ህገ ወጡን ድርጊት ተገቢውን እርምት እንዲሰጥ አሳስቦ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ጭምር