ዜና፡ ታግተው የነበሩት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች በክፍያ ተለቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር፣24/ 2015 ዓ.ም፡- ባልታወቁ ታጣቂዎች ታግተው የነበሩት ቁጥራቸው 20 የሚሆን የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች እያንዳንዳቸው ከ50ሺ ብር እስከ 100ሺ ብር ክፍያ ሰኞ እለት መለቀቃቸውን በጉዳይ በቂ መረጃ ያላቸው አንድ ምንጭ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ። ክፍያውን መፈፀም ያልቻሉ ደግሞ በኋላ ላይ ለመክፈል ቃል በመግባት ተለቀዋል ነው ያሉት ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት ምንጫችን፡፡

ጠለፋው የተፈፀመው ሀሙስ ጥር 18 ቀን 2015 ዓም ከቀኑ 10 ሰዓት 30 አካባቢ ሲሆን ሰራተኞቹ የታገቱት ኩባኒያው ውሃ የሚያገኝበትን የተበላሸ የውሃ ፓምፕ ጣቢያ ለማደስ ስራ ላይ በነበሩበት ወቅት ከሙገር ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው።

የኩባንያው ቃል አቀባይ ሰኞ እለት ለሮይተርስ የዜና አውታር በኢሜል በላከው መግለጫ እንደገለፁት “ሰራተኞቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ነው የተለቀቁት”በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን አዲያ በርጋ ወረዳ የሚገኘው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች ላይ የተፈፀመው ይህ እገታ ለሁለተኛ ግዜ የተከናወነ ሲሆን ባለፈው ዓመት በታህሳስ ወር ታጣቂዎች በተመሳሳይ አካባቢ በኩባንያ አውቶቡስ ውስጥ ሲጓዙ የነበሩ 30 የድርጅቱን ሰራተኞች አግተው ነበር። ታጣቂዎቹ ተጎጂዎችን የለቀቁት ኩባንያው ለእያንዳንዱ ተጎጂ ከ100,000 እስከ 200,000 ብር የሚደርስ ክፍያ በመክፈሉ እንደነበርም ተነግሯል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.