ዜና፡ የምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ እና የሚኒሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በታጣቂዎች መገደላቸውን ተገለፀ
ምስል -ማህበራዊ ሚዲያ አዲስ አበባ፣ ጥር 19/ 2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻከል ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ አቶ አይናለም አላምነህ እና የወረዳው ሚኒሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩት አቶ አዝመራው አማረ በታጣቂዎች መገደላቸውን የዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ። ኃላፊዎቹ በማቻከል ወረዳ ጥር 27/2015 ዓ.ም. ሌሊት ህዝብን ለማገልገል