ዜና፡ በትግራይ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አባቶች በሳምንቱ መጨረሻ በአክሱም ጽዮን የጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5/2015 ዓ.ም፡- በትግራይ ክልል የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አባቶች በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ እና በትግራይ ክልል በሚገኙ የእምነቱ አባቶች በመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መካከል የተፈጠረው ልዩነት