ዜና፡- ባለፈዉ ሳምንት በኦሮሚያ ክልል፣ሰሜን ሸዋ ዞን በታጣቂዎች ከታገቱ 11 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች መሃል ዘጠኙ እስካሁን አለመለቀቃቸው ተገለፀ
አዲስአበባ፣ጥቅምት24/2015 ዓ.ም፡- የታጠቁ ሃይሎች ባለፈዉ ቅዳሜ በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ገብረ ጉራቻ ከተማ የልደታ ማሪያም ቤተክርስቲያን ዲያቆንን ገድለው፣ የደብሩን አስተዳደዳሪ ጨምሮ ሌሎች 11 አገልጋዮችን በማገታቸው፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከትገልፆ ነበር፡፡ ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ቀሲስ ከታገቱት