ዜና፡- ባለፈዉ ሳምንት በኦሮሚያ ክልል፣ሰሜን ሸዋ ዞን በታጣቂዎች ከታገቱ 11 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች መሃል ዘጠኙ እስካሁን አለመለቀቃቸው ተገለፀ

አዲስአበባ፣ጥቅምት24/2015 ዓ.ም- የታጠቁ ሃይሎች ባለፈዉ ቅዳሜ በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ገብረ ጉራቻ ከተማ የልደታ ማሪያም ቤተክርስቲያን ዲያቆንን ገድለው፣ የደብሩን አስተዳደዳሪ ጨምሮ ሌሎች 11 አገልጋዮችን በማገታቸው፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከትገልፆ ነበር፡፡

ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ቀሲስ ከታገቱት 11 አገልጋዮች ውስጥ አስተዳዳሪው እና አንድ አገልጋይ ገንዘብ ተከፍሎ መለቀቃቸውን ነገር ግን ተጨማሪ በሀገረ ስብከቱ የሀርቡ ቦሴ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ አባላት መታገታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል፡፡ 

የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን ሽፈራሁ ለዶቸ ቨለ እንደገለፁት የታገቱ ሰዎችን ለማሰለቀቅ ከፀጥታ አካላት ጋር እየተሠራ ሲሆን፣ በቤተክርስቲያን ላይ ምንም አይነት ጥቃት አልደረሰም ፡፡

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መሰል ተግባራት በአብያተ-ቤተክርስቲያናት ሲፈጸም የመጀመሪያው እንዳልሆነ የገለፁ ሲሆን፣ በዞኑ ስምንት ወረዳዎች ውስጥ በርካታ በሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ሀይማኖታዊ አገልግሎት መስጠት መቆሙንም አክለው ተናግረዋል፡፡

ስማቸው እንዳይገለፁ የፈለጉና የደብሩ አገልጋይ “ድርጊቱ ለገብረ ጉራቻ ከተማ የመጀመሪያ ቢሆንም በአካባቢው ግን እየተለመደ የመጣ ነው” ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጭው በታጣቂውች መታገት እና ገንዘብ መጠየቅ አዲስ ነገር ባይሆንም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ትኩረት ውስጥ መግባታቸው ግን ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አክለውም “የታገቱት አገልጋዮች መወሰዳቸውን እንጂ የወሳጆችንም ሆነ የተወሰዱበትን ስፍራ አናውቅም፡፡ በትንሽ ደመወዝ ለሃይማኖታቸው የቆሙና የሚያገለግሉ አገልጋዮች ላይ መሰል የእገታ ተግባር መፈጸም ግን ገንዘብን ብቻ ፍለጋ አይመስለንም” ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ ከአሶሳ ከተማ ወደ ካማሺ ሲጓዙ የነበሩ ከ16 በላይ መንዶኞች ምዕራብ ወለጋ ውስጥ በምትገኘው ቤንጉዋ በተባለች ስፍራ በታጣቂዎች መታገታቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ መግለፁ ይታወሳል፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሀሚድ ከ16 በላይ ሰዎች መታገታቸውን ለዶቼቬለ ገልፀው ሰዎቹ ከአሶሳ ለጤና ተቋም መድኃኒትና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ጭኖ ወደ ካማሺ ሲያቀና በነበረው ተሽከርካሪ ተሳፍረዉ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ የተጫነው መድኃኒትም በታጣቂዎች መወሰዱንና የታገቱትን ለማስለቀቅ የጸጥታ ኃይሎች ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

አሸከርካሪውን ጨምሮ እስካሁን ከታገቱት መካከል የተለቀቀ ሰው አለመኖሩንም የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሀሚድ አክለዋል፡፡

የታገቱት ሰዎች በብዛት ተማሪዎች እንደሆኑና ሀገር አቀፍ ፈተና ወሰድው እየተመሰሉ እንደነበር አንድ ወንድማቸው መታገቱን ለዶቸ ቨለ የተናገሩ የካማሺ ከተማ ነዋሪም ጠቁመዋል፡፡

ቤንጉዋ ከተማ ከአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ 30 ኪ.ሜ ፣ ከምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማም 20 ኪ.ሜ ቅርብ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.