ዜና ትንታኔ፡ በአማራ ክልል በበርካታ አከባቢዎች የጸጥታ ችግሮች መስተዋላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ፤ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል፣ በረራዎች ተስተጓጉለዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27/2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል በርካታ አከባቢዎቸ የጸጥታ መደፍረስ እየተስተዋለ እንደሚገኝ እና አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። ከሁለት አመት አጋማሽ ጀምሮ ግጭትና ጦርነት በማስተናገድ የሚገኘው የሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ነዋሪዎች በሳምንቱ መጀመሪያ ጀምሮ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ለከተማው ቅርብ በሆኑ የገጠር አከባቢዎች እንደሚሰማ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። ግጭቱ በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት እና በሀገሪቱ የመከላከያ ሀይል መካከል መሆኑን ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል።

የቆቦ ከተማ ነዋሪ የሆነችው እና ስሟ ለደህንነቷ ሲባል እንዳይገለጽ የጠየቀችን ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቀችው ሰኞ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ ጀምሮ በከተማው በቅርብ እርቀት እስከ ንጋት ድረስ የዘለቀ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ እንደነበር ተናግራለች።

ከፍተኛ የሆነ የመከላከያ እንቅስቃሴ መኖሩን የገለጸችልን የከተማዋ ነዋሪ የመከላከያ ሀይሎች በመኪና ላይ የተጠመዱ ትላልቅ መሳሪያዎችን ጭኖ ሲያልፍ መመልከቷን አስታውቃለች።

በተመሳሳይ መንገሻ የተባለ የከተማ ነዋሪ የሆነ ከአዲስ አበባ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በድንገተኛ ሞት የተለየውን ጓደኛውን አስከሬን ይዞ ወደ ሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማ መጓዙን ገልጾ ከአዲስ አበባ በደብረብርሃን ደሴ መንገድ ተጠቅመን እንዳንሄድ መንገዱ በጸጥታ ችግር በመዘጋቱ በአፋር በኩል ዙሪያ ጥምጥም ብዙ ኪሎሜትር እንድንጓዝ ተገደናል ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል። በከተማዋ በዛሬው ዕለትም የባጃጆች እንቅስቃሴ በመከላከያ ወታደሮች መከልከል መጀመሩን ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቋል።

ወደ ክልሉ ከተሞች የሚደረጉ በረራዎች መስተጓጎላቸውን የተመለከቱ መረጃዎችም እየወጡ ይገኛሉ። በላሊበለ ከተማ ዙሪያ በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል ግጭት መካሄዱን እና ወደ ከተማዋ የተደረገ የአውሮፕላን በረራ በዚህም ሳቢያ መስተጓጎሉን ቢቢሲ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። በዛሬው እለት ወደ ጎንደር ሊጓዙ የነበሩ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት በረራው ተሰርዟል መባላቸውን እና ተለዋጭ ቀጠሮ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።

ከክልሉ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ስራ አስፈጻሚ አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ በፌስቡክ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ይህንን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በመልዕክታቸው የአቢይ አሕመድ አስተዳደር በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ወረራና የንፁኃን ግድያ በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስበዋል። የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሚዲያዎች መንግስት የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት ጭምር በአማራ ክልል በከባድ መሣሪያ ታግዞ በንፁኃን ዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ እንድታወግዙና አገዛዙ ላይ ጫና እንድታሳድሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

ሮይተርስ የዜና ወኪል ባሰራጨው ዘገባ በክልሉ እየተስተዋለ ያለው ግጭት በበርካታ አከባቢዎች እየተስፋፋ እንደሚገኝ እና በሰዎች ላይም ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።  የፋኖ አባላት በርካታ ከተሞችን ተቆጣጠሩ የሚሉ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ በመሰራጨት ላይ የሚገኝ ሲሆን ሮይተርስ የዜና ወኪል የዲፕሎማሲ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ታሪካዊቷ ላሊበላ ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር እንደምትገኝ በዘገባው አስታውቋል። የስፔን ኤምባሲ በላሊበላ ከተማ በተለያዩ ምክንያት የገቡ ዜጎቹ ከሆቴል ክፍላቸው እንዳይወጡ የሚያሳስብ መግለጫ ማውጣቱን የዜና ወኪሉ አካቷል። በደብረታቦር በተካሄደ የመከላከያ እና የፋኖ አባላት ግጭት ሶስት ሰዎች በከባዱ ቆስለው አስር ሰዎች ደግሞ ቀላል ጉዳት አስተናግደው ሆስፒታል መታከማቸውን ከሆስፒታሉ ደክተሮች ያገኘውን መረጃ አስታኮ የዜና አውታሩ በዘገባው አስታውቋል። ከሆስፒታሉ ዶክተሮች በተጨማሪ በከተማዋ ከሚገኙ ፖሊሶችም መረጃውን ማረጋገጡን አመላክቷል።

በክልሉ እያገረሸ የመጣውን የጸጥታ ችግር አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አምነው ባለፉት ሁለት ቀናት ባለስለጣናቱ አስተያየት እየሰጡበት ይገኛል።

አቶ ደመቀ መኮንን የፌደራል መንግስቱ ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማህበራዊ ትስስር የፌስቡክ ገጻቸው በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች አሳሳቢ እየሆኑ መጥተዋል ሲሉ ገልጸዋል። አቶ ደመቀ በመልዕክታቸው ብዙ ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ይኖራሉ ሲሉ ገልጸው እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ግን ጠቃሚው መንገድ ሰላማዊና የውይይት አግባብ ነው ብለዋል።

ከዚህ ውጭ ያለው አካሄድ የጥያቄዎቹን መፍቻ መንገድ የሚያደናቅፍ፣ ያለንን የሚያሳጣ፣ በዘላቂነት ሊታዩ ይገባቸዋል የምንላቸውን ጉዳዮች እንዳይፈቱ የሚያወሳስብ አካሄድ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ከለውጡ ብዙ የጠበቅናቸው ግን ደግሞ ምላሽ ያላገኘንባቸው ያላረኩንና ሌሎች ችግሮችና ስሜቶች ይኖራሉ ያሉት አቶ ደመቀ ለእነዚህ ጉዳዮች ቆም ብለን በማሰብ በሰላሙ መንገድ ዘላቂ መፍተሄ እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ ነው ሲሉ ምክራቸውን አቅርበዋል።

የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ በክልሉ “ያለው ግጭት እርስ በእርስ እያገዳደለና ሰብዓዊ ኪሳራ እያደረሰ” መሆኑን ገልፁ፤ “ልዩነት ያለው አካል ሁሉ ነፍጡን አስቀምጦ ወደ ውይይት ይምጣ” ሲሉም ጥሪ ማቅረባቸውን መዘገባችን ይታወሳል። በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳደሩ በክልሉ የፀጥታ ችግር ማጋጠሙን አምነው መንገድ በመዝጋት የሰዎችን እንቅስቃሴ በመግታት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።

እርስ በእርስ በመገዳደል ያመጣነው ለውጥ የለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ አሁን ያለው አካሄድ ክልሉን አደጋ ውስጥ የሚከት በመሆኑ ክልሉን ዋጋ የሚያስከፍል ችግር ከመከሰቱ አስቀድሞ ሁሉም ለሰላም መረባረብ እንደሚገባው አሳስበዋል። 

የሀገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን በኩል ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፉት መልዕክት በ”ፋኖ” ስም እየተንቀሳቀሱ የሃገር ሰላም ለማወክ በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚል አካል ላይ ሰራዊቱ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። በአማራ ክልል በመሬት ላይ ካለው ግጭት የገዘፈ የሚዲያ ትግል ተከፍቷል ብለዋል። ከሰሞኑ በጎንደር የሰሜን ምዕራብ እዝን ዓመታዊ አፈጻጸም ላይ ለመገምገም ወደ ስፍራው እያቀኑ በነበሩ የሰራዊቱ አባላት ላይ ከጩሂት 2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሲደርሱ ተኩስ በሰራዊቱ ላይ መከፈቱን ጠቅሰዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.