ዜና፦አሜሪካ የኤርትራ፣የአማራና፣የአፋር ታጣቂ ሃይሎች ከትግራይ ክልል መውጣት የሰላም ስምምነቱ አካል መሆኑን ገለጸች፤ ስምምነቱ ካልተከበረ ማእቀብ እንደምትጥልም አስጠነቀቀች

በመጋቢት 2014 ዓ.ም የሮይተርስ ጋዜጠኞች ያነሱት ፎቶ የኤርትራ ወታደሮችን በሽረ እና በመቐሌ መካከል ባለ ዋና መንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ ያሳያል

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 7፤ 2015– አሜሪካ የኤርትራ፣የአማራና፣የአፋር ታጣቂ ሃይሎች ከትግራይ ክልል መውጣት በኢትዮጵያ መንግስትና በትግራይ ባለስኅጣናት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት አካል መሆኑን ገለጸች ፡፡ የሰላም ስምምነቱ ካልተከበረ ማእቀብ እንደምትጥል ልታደርግ እንደምትችል አስታወቀች፡፡

አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የስቴት ዲፓርትመንት ባለስልጣን ህዳር 6/2015 ዓም በሰጡት ማብራሪያ የሁለቱ ተደራዳሪ ወገኖች ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በኬኒያ ናይሮቢ ላይ በደረሱበት የሰላም ስምምነቱን የማስፈፀም ሂደት ትጥቅ የማስፈታቱን ተግባር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ያልሆነ በትግራይ ውስጥ የሚገኙ የታጠቁ ሃይሎችን ከማስወጣት ጎን ለጎን የሚፈፀም መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ባለስልጣኑ አያይዘውም “ይህ በጣም ጠቃሚ ነገር ነው ምክንያቱም የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ የመጀመሪያ መተማመን የመጀመሪያው ጥሩ ነገር ሆኖ አሁን ግን ከክልሉ መውጣት እንዳለባቸው መግግባባት ተደርሷል” ብለዋል፡፡

ስምምነቱ የአማራ ልዩ ሃይል እና የአፋር ሚሊሻዎችም ከትግራይ እንዲወጡ አስፍሯል ብለዋል፡፡

የሰላም ስምምነቱን በተገቢው መንገድ ለማስፈፀም አሜሪካ አስፈላጊ ከሆነ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ማእቀብ ልትጥል እንደሚትችል ባለስልጣኑ ተናገረዋል፡፡

አሜሪካ ምንግዜም አስጋዳጅ ነገሮችን ለማስፈፀም ማእቀብን እንደ መሳሪያ ትጠቀማለች በሰብአው መብት ጥሰት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥም ሆነ ይህንን የሰላም ስምምነቱ እንዲከበርና አስገዳጅ እንዲሆን ለማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ማእቀብ ታደርጋለች ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ያልሆኑ ታጣቂዎችን ከትግራይ ማስወጣት የትግራይ ተዋጊ ሃይሎች ጥጥቅ ከማስፈታት ጋር የተያያዘ በመሆኑ የሁለቱም ተደራዳሪ ወገኖች ፍላጎት መሆኑንም ባለስላጣኑ ገልፀዋል፡፡

ለደቂቃም ቢሆን አንተኛም ይልቁንስ ሁለቱ ወገኖች በስምምነታቸው መሰረት ወደፊት እንዲጓዙ ለማድረግ እና በስምምነቱ የተጠቀሱት ሙሉ በሙሉ እስኪፈፀሙ አሜሪካ ድጋፏን ታደርጋለች ብለዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተደረሰው ስምምነት መሰረት የኤርትራ ሰራዊት ከመላው የኢትዮጵያ ድንበርና የአማራ ልዩ ሃይል ከትግራይ መውጣት ወሳኝ እንደሆነም ባለስልጣኑ አስምረውበታል፡፡

ባለስልጣኑ አያይዘውም በተፈረመው የሰላም ስምምነት አንቀፅ 10/4 መሰረት ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን ለማቆምና ችግርኦቻቸውን በአገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት ለመፍታት መስማማታቸው ሰፍሯል በለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ከፓርላማ ጋር በነበራቸው ቆይታ አከራካሪ የሆኑ ቦታዎች በህገ መንግስቱ መሰረት እንደሚፈታ መግለፀቸው ይታወቃል፡፡

ባለስልጣኑ አያይዘውም የሰብአዊ መብት ጥሰትም ተጠያቂነትም በመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ እና በህዋላም በኬኒያ ስምምነት ላይ ልዩ ትኩረት የተሰጠው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

“ለጅምላ የሰብአዊ መብት ጥሰትን በሚመለከት ተጠያቂነት ሊኖር እንደሚገባ የጠቀሱት ባለስልጣኑ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የምርመራና ድጋፍ ሰጭ አካል እንዲኖር ታበረታታለች ፍትሃዊነት የሰፈነበት ሂደት መሆኑ ጠቃሚ ይሆናል” ብልዋል፡፡

ባለስልጣኑ አያይዘውም ለትግራይ ህዝብ ከሚላክ ሰብአዊ ድጋፍ ጋር ተያይዞም ድጋፍ ያለምንም ገደብ መድረስ እንደሚገባው ተናግረዋል ፡፡ ባለስልጣኑ አያይዘውም “ለተጎዱ ወገኖች የሚደረግ ድጋፍ ያለምንም ገደብ መድረስ እንደሚገባው በደቡብ አፍሪካ በተደረገው የሰላም ስምምነት በግኀፅ የተቀመጠ ሲሆን በተጨማሪም በኬኒያው ስምምነት ላይ ይበልጥ ተጠናክሯል”፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.