ዜና፡ ዶ/ር አብይ እና አልሲሲ በፓሪስ ተገናኝተው ደማቅ ፈገግታ የተሞላበት ሰላምታ መለዋወጣቸው በግብጻውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሁኗል

በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በፓሪሱ የፋይናንስ ስብሰባ ተገናኝተው በመጨባበጥ ሰላምታ መለዋወጣቸው እና ፈገግታን መለዋወጣቸው የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል። ለሚዲያዎቹ ትኩረት ዋነኛ ምክንያቱ ኢትዮጵያ እና ግብጽ በህዳሴ ግድብ ሳቢያ ፍጥጫ ላይ ሁነው እያለ የሁለቱ መሪዎች በፈገግታ የተሞላ ሰላምታ መለዋወጣቸው ነው ሲል ሚድልኢስት ሞኒተር በድረገጹ ባስነበበው ዘገባ አስታውቋል።

አልአረቢ የአረብኛ ድረገጽ በጉዳዩ ዙሪያ ባስነበበው ሰፋ ያለ የአረብኛ ዘገባ እንዳመለከተው በግብጽ የሚገኙ ታላላቅ መገናኛ ብዙሃን የሁለቱን መሪዎች በፈገግታ የተሞላበት ሰላምታ በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው ሽፋን ከሰጡ በኋላ እንዲነሳ መደረጉን አስታውቋል። አልአረቢ በድረገጹ ባስነበበው ዘገባ ካይሮ ኒውስ ቻናል፣ ኤክስትራ ኒውስ እና ካይሮ24 የተሰኙ ታላላቅ መገናኛ ብዙሃን የሁለቱን መሪዎች ምስል በልዩ ዘገባነት በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው አሰራጭተው የነበረ ቢሆንም ወዲያውኑ እንዲነሳ መደረጉን የውስጥ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።

በግብጽ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ጉዳዩ መነጋገሪያ መሆኑን ያስታወቀው የለንደኑ አልአረቢ ድረገጽ በሁለት ጎራ እሰጣገባ ማስተናገዱን አመላክቷል። የአልሲሲ ደጋፊዎች ፕሬዝዳንት አልሲሲ ቀውሶችን ለመፈታት የሚጠቀምበት ብልህ አካሄድ ሲሉ እንዳወዱሱት የጠቆመው ዘገባው ሌሎች ደግሞ ኢትዮጵያ ለአራተኛ ግዜ የህዳሴ ግድብ ላይ ውሃ ለመያዝ በይፋ ባሰወቀችበት እና የግብጽን የውሃ ድርሻ ጭራሽ እንደማታከብር በተግባር በማሳየት ላይ እያለች እንዴት እንዲህ አይነት ፈገግታ እያሳዩ አልሲሲ ለዶ/ር አብይ ሰላምታ ይሰጣሉ ሲሉ መተቸታቸውን አመላክቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.