ዜና፡ የአለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ የእርዳታ ስርጭት ጀምሯል መባሉን የትግራይ ባለስልጣን አስተባበሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4/2015 ዓ.ም፡- የአለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል አቋርጦት የነበረውን የምግብ እርዳታ ስርጭት እንደገና ማስጀመሩን ፕሮግራሙ አስታወቀ ሲል አሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል በትላንትናው ዘገባ አመላክቷል፤ ይህንን ዘገባ አስመልክቶ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የክልሉ ባለስልጣናት ግን ጉዳዩን አስተባብለዋል። የትግራይ ክልል የአደጋና ዝግኙነት ኮሚሽን ዋና ሃላፊ ዶ/ር ገብረሂወት ገ/እግዚያበሔር ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ተቋርጦ የነበረው የእርዳታ ስርጭት ተጀምሮ ሳይሆን በክልሉ ሲተገበር የነበረው የምግብ ለስራ ወይንም ሴፍቲኔት ነው የተጀመረው ብለዋል።

የአለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ የጀመረው የሴፍቲኔት ፕሮግራም እንጂ ተቋርጦ የነበረው እርዳታ ስርጭት አይደለም ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል። የሴፍቲኔት ፕሮግራም በትግራይ የተጀመረው ከ19 አመታት በፊት እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ።

ለተጎጂዎች የሚሰጥ እርዳታ ምንም አይነት ግዴታዎች የሌሉት እንዲሁ የሚሰጥ ነው ሲሉ የገለጹት ዶ/ር ገ/ሂዎት የሴፍቲኔት ተጠቃሚ የሚሆኑ ሰዎች ግን በተለያዩ ህዝባዊ ስራዎች ላይ እንዲሳተየፉ በማድረግ የሚሰጥ መሆኑን በንጽጽር አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት የተጀመረው የሴፍቲኔት ፕሮግራም በትግራይ አራት ወረዳዎች ማለትም አስገደ፣ ጽምብላ፣ ታህታይ አድያቦ እና ራያ አዘቦ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል።

የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አቋርጦት የነበረውን የምግብ እርዳታ አቅርቦት በሐምሌ ወር ለመጀመር ማቀዱን የድርጅቱ የፖሊሲ ልማት ክፍል ረዳት ዳይሬክተር ቫለሪይ ጋርኒየሪ ለሮይተርስ ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል። በዘገባችንም ተረጂዎች በመለየቱ ረገድ ሙሉ ለሙሉ በአለም የምግብ ፕሮግራም ቁጥጥር ስር የሚወሰን መሆኑን ስናረጋግጥ ወዲያውኑ እንጀምራለን ማለታቸውን የዜና አውታሩ በዘገባው ማካተቱን እንዲሁም በወረዳ እና በክልሎች አማካኝነት ይወሰን የነበረውን የተረጂዎች ልየታ በማስቀረት የአም የምግብ ፕሮግራም ከአጋሮቹ ጋር በመሆን በራሳቸው መንገድ ተረጂዎችን በመለየት ለመወሰን የሚያስችለውን ሁኔታ እያመቻቹ መሆኑን ማመላከቱም ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም የምግብ ፕሮግራም ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም አመሻሽ ላይ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ለተረጂ ወገኖች የሚያቀርበው እርዳታ በተለያዩ መንገዶች ላልታለመለት አላማ እየዋለ መሆኑን በመግለጽ ሲያቀርብ የነበረውን እርዳታ ላልተወሰ ግዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙሉ በሙሉ ማቆሙን መዘገባችን ይታወሳል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.