ዜና፡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በተናጥል ሁለቱን የሱዳን መሪዎች እየደገፉ መሆናቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30/2015 ዓ.ም፡- ሶስተኛ ሳምንቱን ያስቆጠረው የሱዳን ቀውስ በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል በተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ቢደርሱም ሙሉ ለሙሉ የተተገበረ ስምምነት አልታየም። ሁለቱም ሀይሎች ከጀርባቸው የቆሙ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርጉላቸው ሀገራት መኖራቸው እየተገለፀ ይገኛል። በሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች በስተጀርባ የተሰለፉ የሀገሪቱ አጎራባች ሀገራት በሚል የአለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን በስፋት እያስተጋቡት ያለ አጀንዳ በመሆን ላይ ይገኛል። ይህም የሱዳን ቀውስ የጎረቤት ሀገራትን ጎትቶ በማስገባት የቀጠናው ቀውስ ምንጭ ይሆናል የሚሉ ስጋት የያዙ ትንታኔዎች በስፋት እንዲሰራጭ ምክንያት ሆኗል።

አልጀዚራ በዛሬው እለት ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ይዞት የወጣው እና Will Ethiopia and Eritrea be dragged into Sudan’s complex war?  በሚል ርዕስ እንዳስነበበው ከሆነ ኤርትራ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይልን ለሚመሩት ዳጋሎ ድጋፏን በመስጠት ላይ እንደምትገኝ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ደግሞ የሱዳን ጦር መሪውን አልቡርሃንን። ይህም ሁለቱ ሀገራት የሱዳን ቀውስ ወደ ድንበራቸው ከተጠጋ ለይቶላቸው ጎራ ይዘው መዋጋታቸው እንደማይቀር ማሳያ ነው ሲሉ የአከባቢው ተንታኞች እንደነገሩት አልጀዚራ ባስነበበው ትንታኔ ላይ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በጥር ወር ወደ ሱዳን በማቅናት ከጀነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር መምክራቸውን እና ከሁለት ወራት በኋላ ደግሞ የፈጥኖ ደራሹ ሀይል መሪ ጀነራል ደጋሎ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከሀገሪቱ ፕሬዝዳን ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ማውራታቸውን ዘገባው አስታውሷል።

ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በኋላ በኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር እና በኤርትራው ፕሬዝዳንት መካከል ያለው ግንኙነት የሻከረ መሆኑን ያስታወቀው የአልጀዚራ ተንታኔ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ቅራኔ የገቡት የአማራ ሀይሎች በኤርትራ በመደገፋቸው ሁለቱም ሀገራት ቅራኔያቸው ሰፍቷል ሲል አትቷል።

በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት የሱዳን መንግስት አልፋሽቃ የተባለውን እና በአማራ ገበሬዎች ይታረስ የነበረውን ሰፊና ለም መሬት መቆጣጠሩን ያወሳው ትንታኔው በተመሳሳይ በሱዳን የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ የአማራ ታጣቂዎች ቦታውን ለማስመለስ መሞከራቸው የማይቀር መሆኑን ጠቁሟል። የአማራ ታጣቂ ሀይሎች የገንዘብ እና ወታደራዊ የስልጠና ድጋፍ ከኤርትራ መንግስት በኩል እንደሚደረግላቸው ያመላከተው አልጀዚራ ይህም አሰላለፋቸውን ከዳጋሎ ጋር ማድረጋቸው የማይቀር መሆኑን ያሳያል ብሏል።

አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ገለልተኛ መስለው መቆማቸውን የጠቆመው ዘገባው ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት የሱዳን ቀውስ ወዴት እንዳጋደለ ስላለየለት መሆኑን አስታውቋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.