ዜና፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚደገፈው የናይጀሪያ አየር መንገድ በቀጣይ ጥቅምት ወር ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድጋፍ በመቋቋም ላይ ያለው የናይጀሪያ አየር መንገድ በቀጣይ ጥቅምት ወር ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ። ብሉምበር ቴሌቪዥን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ጣሰውን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው ዘገባ በናይጀሪያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ 49 በመቶ፣ የናይጀሪያ መንግስት አምስት በመቶ እንዲሁም ቀሪው ድርሻ ደግሞ የናይጀሪያ የኢንቨስትመንት ተቋማት እንደሚይዙት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የፌየርፌክስ አፍሪካ ፈንድ ዋና ስራስኪያጅ እንደገለጹለት ጠቁሟል። አቶ ዘመዴነህ 46 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ የሚይዙት የናይጀሪያ የኢንቨስትመንት ተቋማት እነማን እንደሆኑ ከመናገር መቆጠባቸውን ያስነበበው የብሉንበርግ ድረገጽ የናይጀሪያ መንግስት ምንም አይነት ክፍያ እንደማይፈጽም ግን መናገራቸውን አስታውቋል።

የናይጀሪያ አየር መንገድ በአስራ ሁለት የኪራይ አውሮፕላኖች ስራውን እንደሚጀምር ዘገባው አስታውቋል። የናይጀሪያ አየር መንገድ ስራ መጀመር የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጀሪያን ሰማይ ለመቆጣጠር ለሚያደርገው ጥረት ወሳኝ ሚና አለው ያለው ዘገባው በናይጀሪያ ሰማይ ላይ ከሚበሩ 23 የሀገሪቱ አየር መንገዶች ጋር እንደሚፎካከር አመላክቷል።

በናይጀሪያ የአየር መንገድ ስራ መስራት ቀላል አይደለም፤ ብዙ ፈተና ይጠብቀናል ሲሉ አቶ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል ያለው ዘገባው የናይጀሪያን የቢዝነስ ባህል የሚያውቁ ሰዎች በስራችን አሉ እንወጣዋለን እናድጋለን ሲሉ መናገራቸውንም አካቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.