ዜና፡ በአዲስ አበባ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ላይ ያልዋለ 90 ሔክታር መሬት ተመላሽ ተደረገ

ዶ/ር ቀንዓ ያደታ: የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ – ፎቶ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12/2015 ዓ.ም፡- በመዲናዋ 90 ሔክታር የሚሆን መሬት ወስደው ለበርካታ ዓመታት ሳያለሙ አጥረው ካስቀመጡ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ መሬቱ መወሰዱን የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው በሊዝ ዓዋጁ መሠረት ጊዜ ያለፈባቸው በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ 90 ሔክታር መሬቱን ተረክቦ በቅርቡ በሚወጣ ግልጽ ጨረታ ለዓለሚዎች ይተላለፋል ተብሏል፡፡

የመሬት ዋጋ ይጨምራል በሚል እሳቤ መሬት ከወሰዱ በኋላ ከማልማት ይልቅ አጥረው ለረጅም ጊዜ የሚያቆዩ ተቋማትና ግለሰቦች ከተማው ሊያገኝ የሚችለውን ኢኮኖሚዊ ጥቅም አሳጥተውታል ነው የተባለው፡፡

የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀንዓ ያደታ መሬት ተረክበው ግንባታ ጀምረው በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ያሉ ዓለሚዎች ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ድረስ እንዲያጠናቅቁ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ጠቅሰው በቢሮው በኩል ጥብቅ ክትትል የሚደረግ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

የመሬት አስተዳደር ስራው በብዙ ችግሮች የተተበተበ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው የመሬት አስተዳደሩን ዘመናዊ ማድረግ አለመቻሉ ፣ ሌብነትና የመሬት ወረራ፣ ጠንካራ የፍትህ ስርዓት አለመኖር ሕዝቡን በዘርፉ የጸረ ሌብነት ትግል ላይ አለማሳተፍ እና ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስራ አለመሰራቱ መፍትሄ የሚሹ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል፡፡

ችግሮቹን ለመፍታትም ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የቅርብ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑንና  የመሬት አስተዳደሩን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት በካዳስተር የመመዝገብ ስራ መጀመሩን አክለው ገልጸዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.