ዜና፡ በአማራ ክልል ታጣቂዎች የዞን እና ወረዳ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን እንዲሁም ከእስር ቤቶች ታራሚዎችን ማስለቀቃቸውን አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 1/2015 ዓ.ም፡- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መመሪያ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በሰጡት መግለጫ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች “አንዳንድ የዞን እና የወረዳ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን” እንዲሁም በተወሰኑ ቦታዎች “ወንጀለኞችን ከማረሚያ ቤት ማስለቀቃቸውን” አስታወቁ።

በአማራ ክልል እየተከናወነ ያለው የሕግ ማስከበር ሥራ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ክልሉን ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑም ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መመሪያ ዕዝ ችግሩን ለመፍታት ያዘጋጀውን ዕቅድ አፈጻጸም በሚመለከት ውይይት ማድረጉን የሀገሪቱ መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ባሰራጩት ዘገባ አመላክተዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መመሪያ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በሰጡት መግለጫ፤ በክልሉ በተደራጁ ዘራፊ ቡድኖች የተከሰተው የሰላም መደፍረስ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና አስተዳደራዊ ችግሮችን ፈጥሯል ማለታቸውን የጠቀሙት ዘገባዎቹ ዘራፊ ቡድኖች የሕዝብ አግልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎት እንዳይሰጡ ከማስተጓጎል ባሻገር በአንዳንድ አካባቢዎች ማረሚያ ቤቶችን ሰብረው ወንጀለኞችን እንዲያመልጡ እስከማድረግ የደረሰ ውንብድና መፈጸማቸውን ተናግረዋል ብለዋል።

ይህም በተለይ የክልሉ አርሶ አደር የመኸር እርሻ ወቅትን ተረጋግቶ እንዳያከናወን ማድረጉን ጠቅሰው፣ ዜጎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረጉን ተናግረዋል ብለዋል።

ዘራፊ ቡድኑ የሕዝብ መገልገያ ተቋማትን በመዝረፍ እና በማውደም ጭምር የክልሉ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ መሆኑንም ገልጸዋል ያሉት ዘገባዎቹ መንግሥት የትኛውም ጥያቄ በሰላም መፈታት እንዳለበት በጽኑ ያምናል፤ ባለፉት ጊዜያትም ይህንን በተግባር አሳይቷል ማለታቸውን አካተዋል።

በተያያዘ ዜና የመንግስት የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተከትሎ በአማራ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጠቁመው ሁሉም ዜጋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ክልከላ የጣለባቸውን ድርጊቶች ባለመፈጸም ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊነት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የአገልግሎቱ ማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ገጹ ላይ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ አርብ ምሽት፣ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም. በፀጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ተይዘው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው እንዳረጋገጡለት ቢቢሲ በዘገባው አስታውቋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.